ደቡብ ፖሊስ አስረኛ አዲስ ተጫዋቹን አስፈረመ


ደቡብ ፖሊስ አስጨናቂ ፀጋዬን ከአርባምንጭ ከተማ አስረኛ አዲስ ተጫዋች በማድረግ አስፈርሟል፡፡

የተከላካይ አማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ከአርባ ምንጭ ከተማ ወጣት ቡድን ካደገ በኋላ ያለፉትን አራት የውድድር ዓመታት በዋናው የአዞዎቹ ስብስብ ውስጥ ሲጫወት ቆይቶ ለቀጣዩ የውድድር ዓመት ደግሞ በቢጫ ለባሾቹ ቆይታን ለማድረግ አምርቷል፡፡

ደቡብ ፖሊስ ተመስገን ዳናን አዲሱ አሰልጣኝ አድርጎ ከሾመ በኋላ ባለፉት ተከታታይ ቀናት አስር አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል።


© ሶከር ኢትዮጵያ