ኢትዮጵያ ቡና የቀድሞ ተጫዋቹን አስፈረመ

በባቱ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በማድረግ ላይ የሚገኙት ኢትዮጵያ ቡናዎች የቀድሞ ተጫዋቻቸው አዲስ ፍስሀን አስፈርመዋል።

በአሰልጣኝ ዲዲዬ ጎሜስ አሰልጣኝነት ዘመን ከተስፋ ቡድን አድጎ በዋናው ቡድን ጥቂት ጨዋታ የተጫወተው አዲስ በ2011 ውድድር ዓመት ወደ ሰበታ አምርቶ ከቡድኑ ጋር መልካም ጊዜ አሳልፎ ቡድኑ ወደ ፕሪምየር ሊግ እንዲያድግ አስተዎፆ አድርጓል።

ከቡና ጋር በተያያዘ ዜና ለመፈረም ከስምምነት ደርሶ የነበረውና ከክለቡ ጋር ዝግጅት ላይ የቆየው አንዳርጋቸው ይላቅ ፊርማውን ማኖሩ ታውቋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ