የቅዱስ ጊዮርጊስ ወጣት ተጫዋች በውሰት ወደ ደቡብ ፖሊስ አምርቷል

ከቅዱስ ጊዮርጊስ ወጣት ቡድን የተገኘው ሉክ ፓውሊን በውሰት ወደ ደቡብ ፖሊስ ለማምራት አምርቷል፡፡

ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የቅድመ ውድድር ዝግጅትን ሲያደርግ የቆየው ተስፈኛው የአማካይ ስፍራ ተጫዋች በቅዱስ ጊዮርጊስ ከ17 እና ከ20 ዓመት በታች ቡድኖች ተጫወተ ሲሆን ባለፈው የውድድር ዘመን ወደ ዋናው ቡድን ያደገ ቢሆንም ተሳትፎ ሳያደርግ ቀርቷል። ዘንድሮ በከፍተኛ ሊግ መወዳደሩ ዕርግጥ የሆነው ደቡብ ፖሊስም አሰልጣኝ ተመስገን ዳና ለክለቡ የቀረበው የውሰት ጥያቄ ተቀባይነትን በማግኘቱ ቢጫ ለባሾቹን ተቀላቅሏል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ