ዐፄዎቹ ጋናዊውን አጥቂ አስፈረሙ

ጋናዊው ኦሴይ ማዊሊ ለፋሲል ከነማ ፊርማውን አኑሯል።

ባለፈው ዓመት ሃፖል ናዝሬት ሊሊትን ለቆ ወደ መቐለ 70 እንደርታ በመፈረም ከምዓም አናብስት ጋር ጥሩ ዓመት ያሳለፈው የሰላሳ ዓመቱ ጋናዊ አጥቂ አብዛኛው የእግር ኳስ ህይወቱን በእስራኤሎቹ ሃፖል አሽካሎን እና ሃፖል ኢራኒ ኬርያት ሻሞና ያሳለፈ ሲሆን በኢትዮጵያ ቆይታው መቐለ የሊጉን ዋንጫ ሲያነሳ ትልቅ ሚና መጫወቱ ይታወሳል።

ባለፈው የውድድር ዓመት በሁነኛ የአጥቂ ክፍል ተጫዋች እጥረት የተቸገሩት ዐፄዎቹም ቀደም ብለው የናይጀርያዊው አጥቂ ኢዙ አዙካ ውል ማራዘማቸው ሲታወስ ጋናዊውን አጥቂ መፈረም በቦታው አማራጭ ያሰፋላቸዋል ተብሎ ይገመታል።


© ሶከር ኢትዮጵያ