አዳማ ከተማ ዋንጫ | ሀዋሳ ከተማ እና ሀዲያ ሆሳዕና ለፍፃሜ ደርሰዋል

የአዳማ ከተማ ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ዛሬ ሲካሄዱ ወደ ፍፃሜ ያለፉት ቡድኖችም ታውቀዋል።

በ07:00 አዳማ ከተማን ከ ሀዋሳ ከተማ ያገናኘው ጨዋታ በሀዋሳ አሸናፊነት ተጠናቋል። ጨዋታው የመደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ያለ ጎል የተጠናቀቀ ሲሆን አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠው የመለያ ምት ሀዋሳ ከተማ 4-3 አሸንፎ ወደ ፍፃሜው ተሸጋግሯል።

09:00 ላይ በፋሲል ከነማ እና ሀዲያ ሆሳዕና መካከል የተደረገው ጨዋታ በተመሳሳይ በመለያ ምት ሲጠናቀቅ ሀዲያ ሆሳዕና አሸናፊ ሆኗል። ፋሲሎች በ27ኛው ደቂቃ ሙጂብ ቃሲም ባስቆጠረው ጎል ለረጅም ደቂቃዎች መሪ መሆን ቢችሉም በ87ኛው ደቂቃ አማካዩ አብዱልሰመድ ዓሊ ሀዲያን አቻ አድርጎ መደበኛው የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጠናቋል። አሸናፊውን ለመለየት በተሰጡ የመለያ ፍፁም ቅጣት ምቶችም ሆሳዕና 5-4 አሸንፏል።

ውድድሩ በመጪው ቅዳሜ ፍፃሜውን ሲያገኝ በ9:00 ሀዋሳ ከተማ እና ሀዲያ ሆሳዕና ለዋንጫው ይጫወታሉ።


© ሶከር ኢትዮጵያ