የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ፕሪሚየር ሊግ መካከለኛ ዞን 5ኛ ሳምንት ላይ ደርሷል፡፡ ቅዳሜ እሁድ እና ሰኞ በተደረጉት የሊጉ ጨዋታዎች ንግድ ባንክ ወደ መሪነት የወጣበትን ድል ሲያስመዘግብ አአ ከተማ የሳምንቱን ከፍተኛ ድል ወጣቶች አካዳሚ ላይ ተቀዳጅቷል፡፡
ቅዳሜ 8፡00 ላይ የኢትዮጵያ ወጣቶች አካዳሚን የገጠመው አዲስ አበባ ከተማ 5-1 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል፡፡ የአአ ከተማን የድል ግቦች መሃመድ አሚኑ ፣ ተመስገን ዘማ ፣ ፉአድ ነስሩ ፣ ብሩክ ሙሉጌታ እና አሊ አደም ሲያስቆጥሩ የወጣቶች አካዳሚን ግብ ሳሙኤል አበበ ከመረብ አሳርፏል፡፡ በ10፡00 የተካሄደው የሐረር ሲቲ እና መከላከያ ጨዋታ በጦሩ 1-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ የመከላከያን የድል ግብ ከመረብ ያሳረፈው አብነት ይግለጡ ነው፡፡
አሁድ በ9፡00 ኤሌክትሪክ አፍሮ ጽዮንን ስንታየሁ ባስቆጠረው ግብ 1-0 ሲያሸንፍ ቀጥሎ በተደረገው ጨዋታ ደደቢት ቅዱስ ጊዮርጊስን 2-1 አሸንፏል፡፡ የደደቢትን የድል ግቦች ከማል አደም ከመረብ ሲያሳርፍ የቅዱስ ጊዮርጊስን ግብ ዳግማዊ አርአያ ከመረብ አሳርፏል፡፡
ዛሬ በተካሄደ ብቸኛ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኢትዮጵያ ቡናን 1-0 አሸንፎ የሊጉን መሪነት ተቆናጧል፡፡ የሀምራዊዎቹን የድል ግብ ከመረብ ያሳረፈው ታምራት ሲራክ ነው፡፡
የደረጃ ሰንጠረዡ ይህንን ይመስላል፡-
—– 4 ክለቦች የሚሳተፉበት የደቡብ ዞን ፕሪሚየር ሊግ አንደኛ ዙር በሀዋሳ ከተማ መሪነት ባለፈው ሳምንት ተጠናቋል፡፡