የአሰልጣኞች አስተያየት | ፋሲል ከነማ 1-0 ወልዋሎ ዓ/ዩ

በ12ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ፋሲል ከነማ ወልዋሎን 1-0 በሆነ ውጤት ካሸነፈ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች አስተያየታቸውን እንደሚከተለው ሰጥተዋል ።

” በሜዳችን የምንፈልገውን ነጥብ አግኝተናል ” ሥዩም ከበደ (ፋሲል ከነማ)

ስለ ጨዋታው

በጨዋታው የመጀመሪያው አጋማሽ የነበረው ነገር መልካም ነበሪን። ያው ወደፊት መሄድ ያልቻልንበት ነገር እንዳለ ሆኖ ወደፊት እነዛን ነገሮች እናስተካክላለን። በሜዳችን 6ኛ ጨዋታችን ነው ፤ መሪዎች እነመቐለም እየተሸነፉ ነው ፤ እነጊዮርጊስም እየመጡ ነው ያሉት ስለዚህ ይህን ለማስጠበቅ በሙሉ በተጫዋቾችም በኛም ዘንድ ያለው ነገር ይሄ ነው። ያንን አስጠብቆ በመሄድ እና በመጫወት መካከል ያለው ችግር ቢኖርም ከዕረፍት በኋላ የታየው ነገር የሚስተካከል ነው። በአጠቃላይ በሜዳችን የምንፈልገውን ነጥብ አግኝተናል በቀጣዩ ዙር ደግሞ ያለንን ነገር እስጠብቀን ለመሄድ ጊዮርጊስ ፣ መቐለ እና ሀዋሳ ጨዋታ ይቀረናል። እሱን ደግሞ አስተካክለን ለመግባት ጥረት እናደርጋለን ።

ስለ አማካይ ተጫዋቾች ክፍተት

ሀብታሙ ተከስተ ፣ ኦሲ ማውሊ ለመቐለ ጨዋታ ይደርሳሉ። በአንፃሩ ጂብሪል አህመድ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ ይደርሳል። ያለውን ክፍተት ሞልተን እንደርሳልን ፤ ብዙ ተጫዋቾች ከህመም አገግመው እየወጡ ነው። እንደዚህ እየጠጋገንን ከዚህ ደረጃ መድረሱ ሊመሰገን ይገባ ነበር። በአንድ አንድ ደጋፊዎች ላይ የምንሰማው ነገር ሁላችንንም ቅር ያሰኘ ነገር ነው። ተጫዋቾችን በራስ መተማመናቸውን የሚያሳጣ ተግበር ነው እና ይህ ቢስተካከል እና ለቡድኑ ዕድገት በጋራ ብንሰራ ጥሩ ነው ።

ከሜዳ ውጪ ስላለው ውጤት

ከጅማ አባ ጅፋር ጋር በጣም ጥሩ ነበርን ፤ 100% ጥሩ ነበርን። የግብ አጋጣሚዎች እንቢ አሉን እንጅ ህዝቡም በጥሩ ሁኔታ ነው የተቀበለን። በሜዳችንም 100% ውጤት ማንጥልበት ሁኔታ ነው ያለው ሌሎች ነገሮች በሂደት ይስተካከላሉ።

” ውጤቱ ባይገልፀውም ጥሩ እንቅስቃሴ አድርገን ነበር ” አብርሃም ታዓረ (ወልዋሎ ዓ /ዩ)

ስለጨዋታው

ውጤቱ ባይገልፀውም ጥሩ እንቅስቃሴ አድርገን ነበር። በተገኘችው ፍፁም ቅጣት ምት ተሸንፈን ለመውጣት ተገደናል። እንቅስቃሴያችን ግን የተሻለ ነበር። ከሲዳማው ጨዋታ የተጫዋች ለውጥ አላደረግንም ፤ የታክቲክ ለውጥ በማድረግ ግን የተሻለ ተጫውተናል። በመጨረሻም መናገር ምፈልገው የፋሲል ከነማን ደጋፊ ከልብ እናመሰግናለን።

የዋና አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ አለመኖር

ተፅዕኖ አድርጎብናል። በተላይ የሲዳማው ጨዋታ
የተነገረን ለጨዋታው 9 ሰዓት ልንገባ 5 ሰአት ላይ ነበር። ስለዚህ ይህ የራሱ የሆነ ተፅዕኖ ቡድናችን ላይ አሳድሮብናል።

© ሶከር ኢትዮጵያ