ወልዋሎ የቀድሞ ተጫዋቾቹን ደሞዝ ከፍሏል

ካልተከፈለ ደሞዝ ጋር ተያይዞ ከቀናት በፊት በፌደሬሽኑ እገዳ ተጥሎበት የነበረው ወልዋሎ የተጫዋቾቹን ደሞዝ ከፍሎ እገዳው ተነስቷል።

ባለፈው ዓመት በቡድኑ የተጫወቱ ስምንት ተጫዋቾች ደሞዝ አለመከፈል ጋር ተያይዞ በፌዴሬሽኑ እገዳ ተጥሎባቸው የቆዩት ወልዋሎዎች ለተጫዋቾቹ ደሞዝ መክፈላቸውን ከተጫዋቾቹ እና ጉዳዩን ከያዙት የህግ ባለሞያው አቶ ብርሀኑ በጋሻው ማረጋገጥ ችለናል። ክፍያው በቀናት ውስጥ የፈፀሙት ወልዋሎዎች ከተጫዋቾቹ ጋር የነበረውን ውዝግብ መቋጨታቸውን ተከትሎም እገዳው ተነስቶላቸዋል።

በዝውውር መስኮቱ በስፋት ይሳተፋሉ ተብለው የሚጠበቁት ወልዋሎዎች አሰልጣኞች ለመቅጠር በመጨረሻው ሒደት እንደሚገኙ ሲታወቅ ከቅጥሩ በኋላም በርካታ ተጫዋቾች ያስፈርማሉ ተብሎ ይገመታል።

© ሶከር ኢትዮጵያ