የአሰልጣኞች አስተያየት | ወላይታ ድቻ 0-0 ወልዋሎ

ሶዶ ላይ የተደረገው የወላይታ ድቻ እና ወልዋሎ ጨዋታ ያለ ጎል ከተጠናቀቀ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

“ጨዋታ ላይ ጥሩ መንቀሳቀስ ብቻ ውጤት አያስገኝም” ደለለኝ ደቻሳ (ወላይታ ድቻ)

ጨዋታ ላይ ጥሩ መንቀሳቀስ ብቻ ውጤት አያስገኝም። ጨዋታውን ተቆጣጥረን ነበር የተጫወትነው፤ ቢሆንም ያገኘነውን አጋጣሚ መጠቀም ባለመቻላችን ማሸነፍ አልቻልንም። ጎል የማግባት ችግር እንዳለብን ነው ያየነው። ይህንን ችግራችንን ቀርፈን ወደ ማሸነፍ እንመልሳለን። ተጫዋቾቹን እንዳያችሁት በብዛት ወጣቶች ናቸው። ጠንክረን በመስራት ይህንን ችግር መቅረፍ እንችላለን።

” ውጤቱ እንደ ውጤት ጥሩ ነው” ዘማሪያም ወልደጊዮርጊስ (ወልዋሎ)

ጨዋታው በጣም ጥሩ ነበር። ነገር ግን እዚህ ስመጣ ሁልግዜ እንደምለው ሜዳው ለመጫወት ምቹ አይደለም። ለደጋፊው የሚመጥን ሜዳ አይደለም። እንዳያችሁት ለራሳቸው ለድቻዎች ራሱ ለመጫወት አልተመቻቸውም። እኛም አስበን የመጣነውን አጨዋወት እንዳንጫወት አድርጎናል። እንደ ውጤት ካየነው ጥሩ ነው። ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ላይ እየመራን ውጤት ማስጠበቅ ከብዶን ነጥብ ጥለን ነበር። ዛሬ ያንን ችግር ለመቅረፍ ያደረግነው ጥረት ተሳክቶልናል።

© ሶከር ኢትዮጵያ