ፕሮፌሽናል ፉትቦለርስ አሶሴሽን የኮሮና ቫይረስን ለመካለከል የድጋፍ ጥሪ አቀረበ

በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል አቅመ ደካሞችን ለመርዳት ማኀበሩ ለስፖርት ቤተሰቡ የድጋፍ ጥሪ አቅርቧል።

የጤና ባለሙያዎች የሚያስተላልፉትን መልዕክት እንጠብቅ የሚለው ማኅበሩ ጎን ለጎን የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች የሌላቸውን የጎዳና ተዳዳሪዎችን (አቅመ ደካማዎችን) ለመደገፍ የማኅበሩ ጠቅላላ ጉባኤ አባላት እና ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ማኀበራዊ ኃላፊነታችንን እንወጣ ሲሉ እያንዳንዳቸው በግል 300 ሳሙና ለመለገስ የወሰኑ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ይህን በጎ ተግባር ለማገዝ የሚፈልጉ ሌሎች አባላቶች እና የስፖርት ቤተሰቦች ከዛሬ ጀምሮ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሒሳብ ቁጥር ተጠቅመው መደገፍ እንደሚችሉ ተገልጿል፡-

© ሶከር ኢትዮጵያ