መቐለ 70 እንደርታ በአዲስ መንገድ ወደ ልምምድ ሊመለስ ነው

የባለፈው ዓመት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ መቐለ 70 እንደርታዎች በቀጣይ ሰኞ ልምምድ እንደሚጀምሩ ክለቡ አስታውቋል።

ተጫዋቾቹ በየቤታቸው በመሆን በቴሌግራም በሚሰጣቸው ትእዛዞች ይደረጋል የተባለው ይህ የልምምድ መርሀ ግብር ከስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች በተጨማሪም የስነ-ልቦና እና የአመጋገብ ስርዓት እንደሚጨምርም ክለቡ አስታውቋል። ለዚህ እንዲረዳም ሁለት የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ባለሞያዎች ክለቡን ለማገዝ በእንቅስቃሴ ላይ እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል።

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሁሉም ክለቦች ልምምድ ባቆሙበት ሰዓት የከፍተኛ ሊጉ ቡታጅራ ከተማም በተመሳሳይ መንገድ ተጫዋቾቹን ልምምድ እያሰራ መቆየቱ ይታወሳል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ