ሲዳማ ቡና የአማካይ ተጫዋቹ ውልን አራዘመ

የተከላካይ አማካዩ ብርሀኑ አሻሞ በሲዳማ ቡና ውሉን ለማራዘም ከስምምነት ደርሷል፡፡

ከቀናት በፊት የፍቅሩ ወዴሳ፣ ግሩም አሰፋ እና ይገዙ ቦጋለን ኮንትራት ያራዘሙት ሲዳማ ቡናዎች በዛሬው ዕለት የተከላካይ አማካዩን ብርሀኑ አሻሞን ውል ለተጨማሪ ሁለት ዓመት ነው ያራዘሙት፡፡ ከሀዋሳ ታዳጊ ቡድን ተገኝቶ በዋናው ቡድን መጫወት የቻለው ይህ ወጣት አማካይ ሀዋሳን ከለቀቀ በኃላ በደደቢት እና ወልዋሎ ተጫውቶ አሳልፏል፡፡ በያዝነው ዓመት ወልዋሎን ከለቀቀ በኃላ በሲዳማ ቡና ሊጉ እስከተቋረጠበት ጊዜ ድረስ ያገለገለ ሲሆን የአንድ ዓመት ቆይታው በመጠናቀቁ ዛሬ ረፋድ ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት ለመቆየት ፊርማውን በማኖር ተስማምቷል፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ