ሲዳማ ቡና የሁለት ነባር ተጫዋቾችን ውል አራዘመ

ሰንደይ ሙቱኩ እና ሚሊዮን ሰለሞን ለተጨማሪ ዓመታት በክለቡ ለመቆየት ተስማምተዋል፡፡

ዛሬ ረፋድ የተከላካይ አማካይ የሆነው ብርሀኑ አሻሞን ውል ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት ያደሱት ሲዳማዎች አሁንም ሁለት የተከላካይ ሥፍራ ተጫዋቾቻቸውን ለሁለት ተጨማሪ ዓመታት በማደስ ውላቸውን ያራዘሙ ተጫዋቾችን ቁጥር ስድስት አድርሷል፡፡

ኬንያዊው የመሐል ተከላካይ ሰንደይ ሙቱኩ 2009 ላይ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ለሲዳማ ቡና መጫወት የጀመረ ሲሆን በ2010 በድሬዳዋ ከተማ እና ፋሲል ከነማ ያልተሳኩ ጥቂት ቆይታዎችን ካደረገ በኃላ በድጋሚ ወደ ሲዳማ ቡና ተመልሶ እየተጫወተ ይገኛል።

ሌላኛው ውሉን ያራዘመው የመስመር ተከላካዩ ሚሊዮን ሰለሞን ነው፡፡ የቀድሞው የሀምበሪቾ እና አዲስ አበባ ከተማ ተጫዋች በ2011 ወደ ሲዳማ ቡና የመጣ ሲሆን በተሰረዘው የዘንድሮው የውድድር ዓመት ከረጅም ጊዜ ጉዳት በኋላ አገግሞ ወደሜዳ በመመለስ ከመቋረጡ በፊት በነበሩ ሳምንታት ቡድኑን ማገልገል ችሏል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ