ባህር ዳር ከተማ የተከላካዩን ውል አድሷል

እስካሁን የ4 ነባር ተጫዋቾችን ውል ያደሱት የጣና ሞገዶቹ ዛሬ ከሰዓት ደግሞ የተከላካያቸውን ውል አድሰዋል።

በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ የሚመሩት የጣናው ሞገዶች እስካሁን የፍቅረሚካኤል ዓለሙ፣ የዜናው ፈረደ፣ የደረጄ መንግስቱ እና የኃይለየሱስ ይታየውን ውል ለተጨማሪ 2 ዓመት ለማደስ መስማማታቸውን መዘገባችን ይታወሳል። ዛሬ ከሰዓት ደግሞ የቡድኑ የኋላ ደጀን አቤል ውዱ ከክለቡ ጋር ለተጨማሪ 2 ዓመት ለመቆየት ፊርማውን አኑሯል።

በሴንትራል ኮሌጅ የእግርኳስ ህይወቱን የጀመረው አቤል በመቀጠል ወደ አውሥኮድ፣ ደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ፣ እና ፋሲል ከነማ በማምራት ግልጋሎት ሰጥቷል። ይህ ግዙፍ የመሐል ተከላካይ ቡድኑ የመስመር ተጫዋቾችን በጉዳት እና በቅጣት ባጣባቸው ጨዋታዎችም ቋሚ ቦታውን እየቀየረ ሲያገለግል ቆይቷል።

በተያያዘ ዜና የክለቡ የበላይ አመራሮች ከባህር ዳር ከተማ ውጪ የሚገኙ የቡድኑን ነባር ተጫዋቾች ውል ለማደስ በዚህ ሰዓት ወደ አዲስ አበባ እየተጓዙ እንደሆነ የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ ልዑል ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ