ወልቂጤ ከተማ ሁለት ተጫዋቾች አስፈርሟል

ወልቂጤዎች በቀጣይ የውድድር ዓመት ተጠናክረው ለመቅረብ ውል የጨረሱ ተጫዋቾች ውል በማደስ እንዲሁም አዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም የዝውውር መስኮቱ እስኪከፈት ቀድመው የቤት ሥራቸውን እየከወኑ ይገኛሉ። አሁን ደግሞ አቡበከር ሳኒ እና ተስፋዬ ነጋሽን ወደ ቡድናቸው ለመቀላቀል ተስማምተዋል።

አቡበከር ሳኒ ወልቂጤ ከተማን ለመቀላቀል ከተስማሙት አንዱ ነው። ከቅዱስ ጊዮርጊስ ተስፋ ቡድን ተገኝቶ በዋናው ቡድን ለአምስት ዓመታት የተጫወተው አቡበከር በብሔራዊ ቡድንም የተጫወተ ሲሆን በመስመር አጥቂ ስፍራ ላይ በጫላ ተሺታ ላይ ያለውን ጫና ይጋራል ተብሎ ይጠበቃል።

ተስፋዬ ነጋሽ አዳማ ከተማን በመልቀቅ ለቀጣይ ሁለት ዓመት የወልቂጤ መለያን ለማጥለቅ ከስምምነት ደርሷል። ከዚህ ቀደም በወልዲያ እና አዳማ ከተማ የተጫወተው ተስፋዬ ከተከላካይ እስከ አጥቂ ድረስ በተለያዩ ቦታዎች የመጫወት ብቃት ያለው ሲሆን ለወልቂጤ የመስመር እንቅስቅሴ ጎልህ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ