ድሬዳዋ ከተማ አማካይ ተጫዋች አስፈረመ

የተከላካይ አማካይ ስፍራ ተጫዋች የሆነው አስጨናቂ ሉቃስ ወደ ብርቱካናማዎቹ አምርቷል፡፡

የተከላካይ አማካዩ አስጨናቂ ሉቃስ ኢትዮ – ኤሌክትሪክን ከለቀቀ በኃላ ላለፉት ስምንት ዓመታት በሀዋሳ ከተማ መለያ ያገለገለ ሲሆን ከረጅም ጊዜ በኃላ ሀይቆቹን በመልቀቅ በአንድ ዓመት ውል ወደ ድሬዳዋ አቅንቷል፡፡

ዛሬ አንድ ተጫዋች ወደ ክለባቸው የቀላቀሉት አሰልጣኝ ፍሰሀ በቀጣይ ቀናት በተለይ በአጥቂ ሥፍራ የሚጫወቱ ተጫዋቾችን ለማስፈረም በሂደት ላይ መሆኑን ሰምተናል፡፡ ክለቡ ከዚህ ቀደም የሁለት ነባር ተጫዋቾችን ውል ማራዘሙም ይታወሳል፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ