ኢዮብ ዛምባታሮ ወደ ሴሪ ሲ ክለብ አምርቷል

አዲስ አበባ የተወለደው የመስመር ተከላካይ ኢዮብ ዛምባታሮ የሴሪ ሲ ክለብ የሆነው ሞንፓሊን ተቀላቅሏል፡፡

በሴሪ ሲ (ሦስተኛ የሊግ እርከን እየተወዳደረ የሚገኘው ሞኖፖሊ1966 ይፋ እንዳደረገው ከሆነ ተጫዋቹ ክለቡን የተቀላቀለው በውሰት ውል ሲሆን ከዛሬ ጅምሮ ከቡድኑ ጋር ልምምድ ጀምሯል።

የ22 ዓመቱ ኢዮብ ለሁለት ዓመታት በአታላንታ ወጣት ቡድን (ፕሪማቬራ) ቆይቶ በ2018 ወደ ፓዶቫ በውሰት ያመራ ሲሆን ከክለቡ ጋር የሴሪ ሲ ዋንጫን አንስቶ ወደ ሴሪ ቢ መሸጋገር ችሎ ነበር። በቀጣዩ የውድድር ዘመን ደግሞ በጣልያን ሁለተኛው የሊግ እርከን 11 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ የተጫወተ ሲሆን በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ወደ አታላንታ ተመልሶ ከግማሽ ዓመት በኋላ ወደ ራቬና በውሰት በመጓዝ ውድድሩ በኮቪድ 19 ምክንያት እስከተቋረጠበት ጊዜ ድረስ አጭር ቆይታ ማድረግ ችሎ ነበር።

ከዚህ ቀደም ስለ ኢዮብ በሶከር ኢትዮጵያ የቀረበ ዘገባ ፡- LINK

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ