ሀዋሳ ከተማ ተከላካይ አስፈረመ

ምኞት ደበበ ሀዋሳ ከተማን ተቀላቀለ፡፡

የቀድሞው የደደቢት ተጫዋች ያለፉት አራት ዓመታትን በአዳማ ከተማ በመጫወት ድንቅ ጊዜያትን ያሳለፈ ሲሆን ከወራት በፊት ውሉ ከአዳማ ጋር በመጠናቀቁ የቀድሞው አሰልጣኙ አሸናፊ በቀለን ጥሪ ተከትሎ ለሀዲያ ሆሳዕና በነሀሴ ወር አጋማሽ ቅድመ ስምምነት ፈፅሞ የነበረ ቢሆንም በዛሬው ዕለት ግን ለሀዋሳ ከተማ ፊርማውን አኑሯል፡፡

ምኞት ከዝውውሩ በኋላ “ጥሩ ስሜት ነው የተሰማኝ። ከሀዋሳ ጋር ጥሩ ጊዜ እንደማሳልፍ ተስፋ አደርጋለሁ። ከአሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት ጋርም ለመስራት በመምጣቴ እጅግ ደስታን ፈጥሮልኛል።” በማለት ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግሯል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!