የኢትዮጵያ እና ማዳጋስካር ጨዋታ የቀናት ማስተካከያ ተደረገበት

ኢትዮጵያ ከማዳጋስካር የሚያደርጉትን የአፌሪካ ዋንጫ ማጣርያ በተመለከተ ካፍ የኢትዮጵያን ጥያቄ በመቀበል የቀናት ማስተካከያ ማድረጉን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል።

የፌዴሬሽኑ መረጃ ይህንን ይመስላል:-

“ካፍ ይህንን ጨዋታ መጋቢት 18/2013 ለማድረግ ፕሮግራም የላከልን ቢሆንም ኢትዮጵያ ከ ኮትዲቯር የምታካሂደው ጨዋታ መጋቢት 21/2013 በአቢጃን ከተማ የሚካሄድ በመሆኑ ብሔራዊ ቡድናችን በሚያካሂደው የማዳጋስካር እና የአይቮሪ ኮስት ጨዋታ መካከል ያለው የቀናት ልዩነት ጠባብ በመሆኑ የቀን ማስተካከያ መደረግ እንዳለበት ለካፍ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያቀረበውን ጥያቄ የተቀበለው ካፍ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከማዳጋስካር ጋር የሚያከናውነውን ጨዋታ መጋቢት 15/2013 ዓ.ም በባህር ዳር ስታዲየም እንዲካሄድ ውሳኔ አስተላልፏል። ”


© ሶከር ኢትዮጵያ