ኢትዮጵያ ቡና ከ ሀዲያ ሆሳዕና – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

የዛሬውን የረፋድ ጨዋታ የተመለከቱ የመጨረሻ መረጃዎችን እንዲህ እናካፍላችኋለን።

አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ በጅማ የመጨረሻ ጨዋታቸው ሲዳማን በሰፊ የግብ ልዩነት ካሸነፉበት ጨዋታ የአንድ ተጫዋች ቅያሪ ብቻ ሲያደርጉ የመስመር አጥቂው ሀብታሙ ታደሰ በሚኪያስ መኮንም ተተክቷል።

በሀዲያ ሆሳዕና በኩል ደግሞ ሁለት ለውጦች ተደርገዋል። ጉዳት ላይ የሚገኘው ተከላካዩ ቴዎድሮስ በቀለ በሄኖክ አርፌጮ ሲለወጥ ዱላ ሙላቱ ደግሞ የመድሀኔ ብርሀኔን ቦታ ተክቷል።

የቡድኖቹ የዛሬ የመጀመሪያ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል :-

ኢትዮጵያ ቡና

99 አቤል ማሞ
18 ኃይሌ ገብረትንሳይ
4 ወንድሜነህ ደረጄ
2 አበበ ጥላሁን
11 አሥራት ቱንጆ
15 ሬድዋን ናስር
13 ዊልያም ሰለሞን
5 ታፈሰ ሰለሞን
17 አቤል ከበደ
10 አቡበከር ናስር
7 ሚኪያስ መኮንን

ሀዲያ ሆሳዕና

77 መሐመድ ሙንታሪ
2 ሱሌይማን ሀሚድ
5 አይዛክ ኢሴንዴ
25 ተስፋዬ በቀለ
17 ሄኖክ አርፌጮ
23 አዲስ ህንፃ
13 አልሀሰን ካሉሻ
10 አማኑኤል ጎበና
7 ዱላ ሙላቱ
22 ቢስማርክ አፒያ
11 ሚካኤል ጆርጅ


© ሶከር ኢትዮጵያ