ቻምፒየንስ ሊግ፡ ወደ አንደኛውን ዙር የተቀላቀሉ 32 ክለቦች ታውቀዋል 

የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ቅድመ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ ተደርገዋል፡፡ በአብዛኞቹ ጨዋታዎች የተጠበቁት ክለቦች ወደ አንደኛው ዙር አልፈዋል፡፡ የኢትዮጵያ ተወካዩ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሲሸልሱን ሴንት ሚሸልን 4-1 በሆነ የአጠቃላይ ውጤት አሸንፏል፡፡ የዩጋንዳው ቫይፐርስ በናይጄሪያው ኢኒየምባ 2-1 ተሸንፎ ከውድድሩ ውጪ ሆኗል፡፡ ሌላው የምስራቅ አፍሪካ ክለብ ጎር ማሂያ በማዳጋስካሩ ሲኤንኤፒኤስ ስፖርትስ 3-1 ተሸንፎ ከቻምፒየንስ ሊጉ በግዜ ተሰናብቷል፡፡ ስታደ ማሊያን፣ ኤኤስ ቪታ ፣ ክለብ አፍሪካ፣ ካይዘር ቺፍስ፣ ማሌሎዲ ሰንዳውንስ፣ አሴክ ሚሞሳ እና ኤምኦ ቤጃ ወደ ተከታዩ ዙር ያለፉ የተወሰኑ ክለቦች ናቸው፡፡ የብሩንዲው ቪታሎ ክለብ ሊኦሊን ከሜዳው ውጪ ባገባው አንድ ግብ ታግዞ በማሸነፍ ወደ አንደኛው ዙር አልፏል፡፡ በመጀመሪያው ዙር ከአሁኑ ተጠባቂ ሆኑ ጨዋታዎች ያሉ ሲሆን ጨዋታዎቹ በመጋቢት ወር ይካሄዳሉ፡፡ በዋይዳድ ካዛብላንካ እና ኤኤስ ዱዋአነስ መካከል ሊደረግ የነበረው የመልስ ጨዋታ ሌላ ግዜ በመታዘሙ ሳይካሄድ ቀርቷል፡፡ ዋይዳድ በመጀመሪያው ጨዋታ 2-0 አሸናፊ ነበር፡፡ የሁለቱ ቡድኖች አሸናፊ በመጀመሪያው ዙር ሲኤንኤፒኤስ ስፖርትስን ይገጥማል፡፡

የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች

ቅዱስ ጊዮርጊስ (ኢትዮጵያ) ከ ቲፒ ማዜምቤ (ዲ.ሪ. ኮንጎ)

ዋሪ ዎልቭስ (ናይጄሪያ) ከ አል ሜሪክ (ሱዳን)

ኤቷል ደ ኮንጎ (ኮንጎ ብራዛቪል) ከ ኢኤስ ሴቲፍ (አልጄሪያ)

አል አሃሊ ትሪፖሊ (ሊቢያ) ከ አል ሂላል (ሱዳን)

ኤኤስ ቪታ ክለብ (ዴ.ሪ. ኮንጎ) ከ ክለብ ፌሮቫያሪዮ ዲ ማፑቶ (ሞዛምቢክ)

ማሜሎዲ ሰንዳውን (ደቡብ አፍሪካ) ከ ኤሲ ሊዮፓርድስ (ኮንጎ ብራዛቪል)

ስታደ ማሊያን (ማሊ) ከ ኮተን ስፖርት (ካሜሮን)

ኤፒአር (ሩዋንዳ) ከ ያንጋ አፍሪካ (ታንዛኒያ)

ሲአርዲ ዱ ሊቦሎ (አንጎላ) ከ አል አሃሊ (ግብፅ)

ክለብ አፍሪካ (ቱኒዚያ) ከ ኤምኦ ቤጄ (አልጄሪያ)

ኦኤስ ኮሪብጋ (ሞሮኮ) ከ ኤቷል ደ ሳህል (ቱኒዚያ)

ዜስኮ ዩናይትድ (ዛምቢያ) ከ ሆሮያ ኮናክሬ (ጊኒ)

ኢኒያምባ (ናይጄሪያ) ከ ቪታሎ (ቡሩንዲ)

ዩኒየን ዱዋላ (ካሜሮን) ከ ዛማሌክ (ግብፅ)

ካይዘር ቺፍስ (ደቡብ አፍሪካ) ከ አሴክ ሚሞሳ (ኮትዲቯር)

ሲኤንኤፒኤስ ስፖርትስ (ማዳጋስካር) ከ ዋይዳድ ካዛብላንካ (ሞሮኮ) / ኤኤስ ዱዋአኔስ (ሴኔጋል)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *