አዳማ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ : ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

አዳማ ከተማ 2-3 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

78′ ታፈሰ ተስፋዬ

90+1′ አቢኮዬ ሻኪሩ

36′ 67′ ጋብሬል አህመድ

69′ ፍቅረየሱስ ተ/ብርሃን

 

ተጠናቀቀ
ጨዋታው በንግድ ባንክ 3-1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

90+1 ጎልልል!!!
አዳማ ከተማ

አቢኮዬ ሻኪሩ ከሱሌማን የተሻገረለትን ኳስ ወደ ግብነት ቀይሮታል

90′ መደበኛው የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጠናቆ 4 ደቂቃ ተጨመረ

78’ጎልልል!!! አዳማ ከተማ
ታፈሰ ከፋሲካ የተሻገረለትን ኳስ ተጠቅሞ የአዳማን የመጀመርያ ግብ አሰቆጠረ

*ጨዋታው ሀይል የተቀላቀለቀት እየሆነ መጥቷል፡፡ ከባንክ ጋብሬል አህመድ እና ቢንያም በላይ ከአዳማ ምንተስኖቸ፡ት ከበደ የማስጠንቀቅያ ካርድ አይተዋል፡፡

69′ ጎልልል!!! ንግድ ባንክ
ፍቅረየሱስ ተክለብርሃን 3ኛውን ደገመ!
በረጅሙ የተላከለትን ኳስ የአዳማ ተከላካዮችን በማምለጥ በሲሳይ መረብ ላይ አሳርፎታል፡፡
የአዳማ ከተማ ደጋፊዎች ሜዳውን ለቀው መውጣት ጀምረዋል፡፡

67′ ጎልልል!!! ንግድ ባንክ
ጋብሬል አህመድ
የተሻማውን የማእዘን ምት ወደ ግብነት ቀይሮታል፡፡

68′ ጋብሬል አህመድ በግምት ከ35 ሜትር አክርሮ የመታውን ኳስ ሲሳይ ባንጫ አውጥቶታል፡፡

66′ የተጫዋች ለውጥ – ንግድ ባንክ
ሰለሞን ገብረመድህን ወጥቶ አምሃ በለጠ ገብቷል፡፡

56′ ታፈሰ ሻኪሩ ከመስመር ያሻገረለትን ኳስ ተጠቅሞ አስቆጠረ ተብሎ ሲጠበቅ በግቡ አናት ሰዶታል

ተጀመረ
2ኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡

የእረፍት ሰአት ቅያሪ – አዳማ ከተማ
ዲሚጥሮስ ወልደስላሴ እና ብሩክ ቃልቦሬ ወጥተው ወንድሜነህ ዘሪሁን እና ፋሲካ አስፋው ገብተዋል፡፡
– – – – –

ተጠናቀቀ
የመጀመርያው አጋማሽ በንግድ ባንክ መሪነት ተጠናቋል፡፡

45′ መደበኛው የመጀመርያ አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 3 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

36’ጎልልል!!! ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ቢንያም በላይ ከረጅም ርቀት የመታውን ኳስ ሲሳይ በአግባቡ መቆጣጠር ባለመቻሉ ያገኘውን ኳስ ተጠቅሞ ጋብሬል አህመድ ባንክን ቀዳሚ አድርጓል፡፡

በዛሬው ጨዋታ ፌቮ ኢማኑኤል እና አንተነህ ገብረክርስቶስ አምና የተጫወቱበትን አዳማ ከተማ በተቃራኒው በመግጠም ላይ ይገኛሉ

20′ ጨዋታው ቀጥሏል፡፡ አንተነህ ከሜዳ ውጪ ህክምና ማድረጉን ቀጥሏል፡፡

17′  አንተነህ አየር ላይ የመጣ ኳስ ለመምታት ሲሞክር በጀርባው ወድቋል፡፡ በአሁኑ ሰአት ጨዋታው ተቋርጦ የህክምና እርዳታ እየተደረገለት ይገኛል፡፡

16′  ደሳለኝ ደባሽ በአንድ ሁለት ቅብብል ወደ ውስጥ ገብቶ የሞከረው ኳስ ኢማኑኤል አውጥቶበታል፡፡

*በአዳማ አበበ ቢቂላ የተገኘው ተመልካች ከወትሮው በተለየ መልኩ ቀንሶ ታይቷል፡፡

3′ አዳማ የመጀመርያውን የግብ ሙከራ በሻኪሩ አማካኝነት አድርጓል፡፡ ከታከለ ያገኘውን ኳስ ወደ ፍፁም ቅጣት ምት ክልል ጠርዝ ገፍቶ የመታው ኳስ ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

1′ ጨዋታው ተጀመረ
አዳማ ከተማን ለረጅም አመት ሲደግፍ የቆየው ዳንኤል የተባለ ደጋፊን ህልፈት ለማሰብ የ1ደቂቃ የህሊና ፀሎት ተደርጎ ጨዋታው ጀምሯል፡፡

 

08፡50 ሁለቱም ቡድኖች እንዲሁም ጨዋታውን የሚመሩት ዳኞች ሜዳ ገብተው ሰውነታቸውን በማፍታታት ላይ ይገኛሉ፡፡

 

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሰላለፍ

ኢማኑኤል ፌቨር

ዳንኤል አድሃኖም – ቢንያም ሲራጅ – አቤል አበበ – አንተነህ ገብረክርስቶስ

ጋብሬል መሃመድ – ሰለሞን ገብረመድህን

ኤፍሬም አሻሞ – ፍቅረየሱስ ተክለብርሃን – ቢንያም በላይ

ቢንያም አሰፋ

 

የአዳማ ከተማ አሰላለፍ

ሲሳይ ባንጫ

ምንተስኖት ከበደ – ዲሜጥሮስ ወልደስላሌ – ሞገስ ታደሰ – ሱሌማን መሃመድ

ብሩክ ቃለቦሬ – ደሳለኝ ደባሽ – ወንድወሰን ሚልኪያስ

ታከለ አለማየሁ – ታፈሰ ተስፋዬ – አቢኮዬ ሻኪሩ

 

እንደምን ውላችኋል ክቡራት እና ክቡራን!!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 12ኛ ሳምንት አዳማ አበበ ቢቂላ ላይ አዳማ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚያደርጉት ጨዋታ 09፡00 ላይ ይጀምራል፡፡ ጨዋታውን በቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት በዚሁ ገፅ ላይ እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡

አብራችሁን ቆዩ!text-align: center;color: #ff0000;

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *