ሁለት ተከላካዮች ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጠርተዋል

ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ዝግጅት እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለሁለት የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቾች ጥሪ ማድረጉን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ጥሪ ያደረጉላቸው ተጫዋቾች የኢትዮጵያ ቡናው ወንድሜነህ ደረጀ እና የሰበታ ከተማው መሳይ ጳውሎስ ናቸው። መሳይ ከዚህ ቀደም ከኒጀር ጋር ለተካሄዱት ጨዋታዎች ዝግጅት ተጠርተው ከነበሩ ተጫዋቾች አንዱ የነበረ ሲሆን ወንድሜነህ ከዚህኛው ምርጫ በቀር በሌሎቹ ላይ በስብስብ ውስጥ የነበረ ተከላካይ ነው።

ዋልያዎቹ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ማዳጋስካርን ረቡዕ መጋቢት 15 ባህር ዳር ላይ ሲያስተናግዱ ከአምስት ቀናት በኋላ ደግሞ አቢጃን ላይ የምድቡ የመጨረሻ ጨዋታቸውን ከአይቮሪኮስት ጋር ያደርጋሉ።


© ሶከር ኢትዮጵያ