ሉሲዎቹ ስብስባቸውን ይፋ አድርዋል

በአሠልጣኝ ብርሃኑ ግዛው የሚመሩት ሉሲዎቹ ከደቡብ ሱዳን ጋር ለሚያደርጉት የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ስብስባቸውን ይፋ አድርገዋል።

ከፊቱ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች የሚጠብቀው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከጨዋታዎቹ በፊት አቋሙን ለመፈተሽ የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ቀጠሮ ይዟል። በዚህም ቡድኑ ከሚያዝያ 2-5 ድረስ ከደቡብ ሱዳን ጋር ይጫወታል። የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሠልጣኝ ብርሃኑ ግዛውም በአቋም መፈተሻ ጨዋታው ላይ የሚጠቀሟቸውን ተጫዋቾች ይፋ አድርገዋል። ስበብስቡም የሚከተለውን ይመስላል:-

ግብ ጠባቂዎች

ንግስት መዓዛ (ንግድ ባንክ)፣ እምወድሽ ይርጋሸዋ (አዳማ ከተማ)፣ ታሪኳ በርገና (መከላከያ)

ተከላካዮች

ታሪኳ ደቤሶ፣ ብዙዓየሁ ታደሰ፣ ዓለምነሽ ገረመው (ንግድ ባንክ)፣ ፅዮን እስጢፋኖስ (መከላከያ)፣ ትዝታ ኃ/ሚካኤል (ሀዋሳ ከተማ)፣ አብነት ለገሰ (አአ ከተማ)፣ ሀሳቤ ሙሶ (ድሬዳዋ ከተማ)

አማካዮች

እመቤት አዲሱ (ንግድ ባንክ)፣ እፀገነት ግርማ (ጌዴኦ ዲላ)፣ እፀገነት ብዙነህ (ኤሌክትሪክ)፣ ሲሳይ ገ/ዋህድ (ኤሌክትሪክ)፣ ማዕድን ሳህሉ (ድሬዳዋ)፣ የምስራች ሞገስ (አካዳሚ)

አጥቂዎች

ሎዛ አበራ፣ አረጋሽ ካልሳ፣ ሰናይት ቦጋለ (ንግድ ባንክ)፣ ሴናፍ ዋቁማ (መከላከያ)፣ መሳይ ተመስገን (ሀዋሳ ከተማ)፣ መሳይ ተመስገን (መከላከያ)፣ ነፃነት መና (ሀዋሳ ከተማ)፣ ዮርዳኖስ ምኡዝ (ኤሌክትሪክ)፣ ንግስት በቀለ (አካዳሚ)፣ ቤዛዊት ንጉሤ (አቃቂ ቃሊቲ)


© ሶከር ኢትዮጵያ