ሀዋሳ ከተማ 2-1 ቅዱስ ጊዮርጊስ
54′ ፍርዳወቅ ሲሳይ : 90+2 አስቻለው ግርማ
78′ ደጉ ደበበ
ተጠናቀቀ
ጨዋታው በሃዋሳ ከተማ 2-1 አሸናፊነት ተጠናቀቀ
90+4′ የማእዘን ምት ሊሻማ የወጣው ኦዶንካራ የተሻማውን ኳስ በግንባሩ ገጭቶ ቢሞክርም ለትንሽ ወትቶበታል፡፡
*ሮበርት ኦዶንካራ የማእዘን ምት ሊሻማ ወደ ሀዋሳ የግብ ክልል ሄዷል፡፡
ግቧን አመቻችቶ ያቀበለው ደስታ ዮሃንስ ማልያውን አውልቆ በመጨፈሩ 2ኛ ቢጫ ካርድ ተመልክቷል፡፡
አስቻለው ግርማ ከደስታ ዮሃንስ የተሻገረለትን ኳስ በግንባሩ በመግጨት ሀዋሳን መሪ አድርጓል፡፡
90′ መደበኛው የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጠናቆ 4ኛ ዳኛው ተጨማሪ 5 ደቂቃ አሳይተዋል፡፡
84′ አስጨናቂ ሉቃስ የመታው ኳስ ቋሚ ለትሞ ሲመለስ አንተነህ አግኝቶተ አገባው ተብሎ ሲጠበቅ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡
አንተነህ ተሻገር ገብቶ ፍርዳወቅ ሲሳይ ወጥቷል፡፡
ተቀይሮ የገባው አቡበከር ሳኒ የማስጠንቀቅያ ካርድ ተመልክቷል፡፡
በሃይሉ አሰፋ ያሻማውን ቅጣት ምት ደጉ ደበበ በግንባሩ በመግጨት ቅዱስ ጊዮርጊስን አቻ አድርጓል፡፡
አቡበከር ሳኒ ገብቶ ራምኬል ሎክ ወጥቷል፡፡
ደሰታ ዮሃንስ ኳስ አላግባብ አባክኗል በሚል የማስጠንቀቅ ካርድ ተመልክቷል፡፡
አስጨናቂ ሉቃስ ገብቶ ሃይማኖት ወርቁ ወጥቷል
አይዛክ ኢሴንዴ ወጥቶ ምንተስኖት አዳነ ገብቷል፡፡
54′ ጎልልል!!! ሀዋሳ ከተማ
ፍርዳወቅ ሲሳይ ከደስታ ዮሃንስ የተሻገረለትን ኳስ ተጠቅሞ ሀዋሳ ከተማን መሪ አድርጓል፡፡
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀመረ
የእረፍት ሰአት ቅያሪ
ተስፋ ኤልያስ ወጥቶ ዮሃንስ ሌሌቦ ገብቷል፡፡
ተጠናቀቀ
የመጀመርያው አጋማሽ ካለግብ ተጠናቋል፡፡
45′ የመጀመርያው አጋማሽ መደበኛ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 4ኛ ዳኛው ተጨማሪ 1 ደቂቃ አሳይተዋል፡፡
32′ ሀዋሳ ከተማዎች ኳሱን በመቆጣጠር ብልጫ ቢያሳዩም ወደ ግብ እድልነት መለወጥ አልቻሉም፡፡
አዳነ ግርማ ሃይማኖትን ለመንጠቅ ሃይል ተጠቅሟል በሚል የማስጠንቀቅያ ካርድ ተመልክቷል፡፡
26′ ሀዋሳ ከተማ ጫና ፈጥሮ እተንቀሳቀሰ ነው፡፡ ፍርዳወቅ ሲሳይ እና ሙሉጌታ ምህረት ግብ ለማስቆጠር የሚቀሉ ኳሶችን አምክነዋል፡፡
20′ አስቻለው ከመስመር እየገፋ ወደ መሃል በመግባት የሞከረውን ኳስ ሮበርት ወደ ውጪ አውጥቶታል፡፡
18′ አዳነ ግርማ ከመስምር የተሻገረለትን ኳስ አንድ ተጫዋች በማለፍ ሞክሮ ግብ ጠባቂው አውጥቶበታል፡፡
አሉላ ግርማ የማስጠንቀቅያ ካርድ ተመልክቷል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ3 ደቂቃዎች ልዩነት 3 የማስጠንቀቅያ ካርድ ተመዞበታል፡፡
በኃይሉ አሰፋ ኳስ በእጁ በመንካቱ አርቢቴር ዘካርያስ ግርማ ቢጫ ካርድ አሳይተውታል፡፡
አይዛክ ኢሴንዴ በአስቻለው ግርማ ላይ በሰራው ጥፋት ማስጠንቀቅያ ካርድ ተመልክቷል፡፡
11′ ጨዋታው መልካም እንቅስቃሴ እየታየበት ቢሆንም ሁለቱም ቡድኖች ሃይል ቀላቅለው በመጫወት ላይ ናቸው
፡፡
ተስፋ ኤልያስ በአስቻለው ታመነ ላይ በሰራው ጥፋት የመጀመርያውን የማስጠንቀቅያ ካርድ ተመልክቷል
4′ ሙጂብ ቃሲም በግምት ከ40 ሜትር ርቀት አክርሮ የመታውን የቅጣት ምት ሮበርት በጥሩ ሁኔታ ይዞበታል፡፡
2′ ፍርዳወቅ ሲሳይ ከመስመር የተሻገረለትን ኳስ በግንባሩ ገጭቶ ቢሞክርም ወደ ውጪ ወጥቶበታል
የሀዋሳ ከተማ አሰላለፍ
ዳንኤል ደርቤ – ሙጂብ ቃሲም – ግርማ በቀለ – ደስታ ዮሃንስ
ተስፋ ኤልያስ – ሙሉጌታ ምህረት – ኃይማኖት ወርቁ
ኤፍሬም ዘካርያስ – ፍርዳወቅ ሲሳይ – አስቻለው ግርማ
የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰላለፍ
አይዛክ ኢሴንዴ – ደጉ ደበበ – አስቻለው ታመነ – አበባው ቡታቆ
ምንያህል ተሸመ – ናትናኤል ዘለቀ – አሉላ ግርማ
በኃይሉ አሰፋ – አዳነ ግርማ – ራምኬል ሎክp style=