የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ማጣርያ ፡ አልጄርያ ከ ኢትዮጵያ 

አልጄርያ 1-0 ኢትዮጵያ 

የአፍሪካ ዋንጫ 1ኛ ዙር ማጣርያ

ሀማዲ ስታድየም

ተጠናቀቀ!
ጨዋታው በአልጄርያ 1-0 አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡ የመልሱ ጨዋታ ከ15 ቀናት በኀላ አአ ላይ ይደረጋል፡፡

81′ የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ
ብርቱካን ገብረክርስቶስ ወጥታ ረሂማ ዘርጋ ገብታለች፡፡

74′ ህይወት በግምት ከ40 ሜትር የመታችውን ቅጣት ምት ታክኒት ይዛባታለች፡፡ ታክኒት የሚመቱባትን ኳሶች በአግባቡ መቆጣጠር ሲቸግራት በተደጋጋሚ ተስተውሏል፡፡

67′ የተጫዋች ለውጥ – አልጄርያ
ኢማን ማሩች ገብታ ባራ ፋቲማ ወጥታለች፡፡

65′ ብሩክታዊት የግብጠባቂዋን ከግበ ቧመውጣት ተመልክታ በግሩም ሁኔታ የሞከረችውን ኳስ ቲክሪት እንደምንም አውጥታዋለች፡፡

63′ ከቅጣት ምት የተሻገረውን ኳስ ባራ ፋቲማ ሞክራ ፅዮን እስጢፋኖስ አውጥታባታለች፡፡

61′ ጎልልል!!!! አልጄርያ
ዜሮኬ አልጄርያን ቀዳሚ ያደሰገች ግብ በግሩም ሁኔተታ አስቆጥራለች፡፡

59′ ሎዛ ከፍፁም ክታት ምት ክልል ውጪ ወደ ግብ የሞከረችው ኳስ አግዳሚውን ለትሞ ወጥቷል፡፡

55′ በሁለተኛው አጋማሸ ኢትዮጵያ ወደ ጎል በመድረስ በኩል ተሽላለች፡፡

ተጀመረ
2ኛው አጋማሽ ተጀምሯል፡፡ ኢትዮጵያ ከግራ ወደ ቀኝ ስታጠቃ አልጄርያ በተቃራኒው ታጠቃለች፡፡
——-
ተጠናቀቀ!
የመጀመርያው አጋማሽ ካለግብ ተጠናቋል፡፡

45′ ከቅጣት ምት የተሻገረውን ኳስ ነኢማ ቦሂኔ ብተታስቆጥርም ከጨዋታ ውጪ ተብሎ ተሽሯል፡፡

42′ ብሩክተታዊት በረጅሙ የላከችውን ኳስ ታክኒት ካሂና በአግባቡ መቆጣጠር ባትችልም በቅርብ ርቀተ ትየነበረችወ ውሎዛ ሳትደርስበት ቀርታለች፡፡

37′ ዳግማዊት ጉዳት ደርሶባት የህክምና እርዳታ እየተደረገላት ይገኛል፡፡ ሉሲዎቹ ሙቀቱ የከበዳቸው ይመስላል፡፡

35′ አሁን ጨዋታው ተመጣጣኝ እንቅስቃሴ እየተደረገበት ነው፡፡ አልጄርያዎች ወደፊት በመሄድ የተሻሉ ቢሆኑም አስደንጋጭ የሚባል የግብ ሙከራ አላደረጉም፡፡

21′ ሽታዬ ያሻማችውን ቅጣት ምት ህይወት በግንባሯ ገጭታ ወደ ውጪ ወጥቶባታል፡፡
ኦማር ሃምዲ ስታድየም ከጥቂት ሴት ተመልካቾች በቀር ባዶ ሆኗል፡፡

18′ ብሩክታዊት ግርማ ጉዳት ደርሶባት የህክምና እርዳታ እየተደረገላት ይገኛል፡፡

14′ ሎዛ አበራ በፊት መስመር ከቡድኑ ተነጥላለች፡፡ ኢትዮጵያ እስካሁን የግብ ሙከራ ማድረግ አልቻለችም

7′ ቤንላዛር ከርቀት የሞከረችው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡ አልጄርያዎች በኳስ ቁጥጥርም ሆነ በጎል ሙከራ የበላይነቱን ይዘዋል፡፡

6′ ቦሄኒ ከቅጣት ምት የተሻገረ ኳስ ሞክራ ወደ ውጪ ወጥቶባታል፡፡

4′ አልጄርያዎች የመጀመርያ ጎላቸውን ለማስቆጠር ተቃርበው ነበር፡፡ ወደ ኢትዮጵያ የግብ ክልል በቀላሉ እየደረሱ ነው፡፡

1′ ጨዋታው ተጀምሯል፡፡

soccer-4-icon የመጀመርያ ተሰላፊዎች የሚከተሉት ናቸው፡-

ዳግማዊት መኮንን

መስከረም ኮንካ – ጥሩአንቺ መንገሻ – ፅዮን እስጢፋኖስ – እፀገነት ብዙነህ 

ኤደን ሽፈራው – ህይወት ደንጊሶ

ብርቱካን ገ/ክርስቶስ (አ) – ብሩክታዊት ግርማ – ሽታዬ ሲሳይ 

ሎዛ አበራ

©ዳግም ዝናቡ (ልሳን ለሴቶች ስፖርት)

–    –    –    –    –
የአልጄርያ አሰላለፍ

ታክኒት ካሂና

ሜሳዎር ፋይዛ – ባራ ፋቲማ – አርቢ ኦዉዳ – ሴኮአን ፋቲማ (አ)

ቤንላዛ ሚርያም – ሳዶ ሀቢባ – ሰብሪና ኦመር – ነኢማ ቦሂኒ

ሶፍያ ጉላቲ – ዳልያ ዜሮኪ

– – – – –

የአልጄርያውያን አስተያየት 

የአልጄርያ ዋና አሰልጣኝ አዚድ ቺህ በቡድናቸው ዙርያ ለጋዜጠኞች በሰጡት አስያየት ጨዋታውን ለማሸነፍ እንደተዘጋጁ ተናግረዋል፡፡ ” ሂሳባዊ ሰሌት ውስጥ መግባት አንፈልግም፡፡ በሃይል እና ፈጣን አጨዋወት ጨዋታውን እዚሁ ለመጨረስ ተዘጋጅተናል፡፡” ብለዋል፡፡ 2861997 ነኢማ ቦሄኒ ፡ “ጥሩ ዝግጅት አድርገናል፡፡ በመልካም አቋም እና ዝግጁነት ላይ እንገኛለን፡፡ ለዚህ ጨዋታ በርካታ ተጫዋቾች ከፈረንሳይ መጥተው ተቀላቅለውናል፡፡ ለአፍሪካ ዋንጫ እንድናልፍ ይረዱናል ብለን እናስባለን”

ከፈረንሳዩ አውሪላስ ክለብ የተመረጠችው ያስሚን ቢያውፍራ በበኩሏ ለመጀመርያ ጊዜ ቡድኑን ስትቀላቀል በተደረገላት አቀባበል መደሰቷለ፡ን ገልፃለች” በተደረገልኝ አቀባበል ተደስቻለሁ፡  እኔን ጨምሮ ቡድናችን በፈረንሳይ የተለያዩ ክለቦች አጨዋወት ውስጥ ያለፉ ተጫዋቾች ስብስብ ቢሆንም በጥሩ ሁኔታ ተዋህደናል፡፡ ጨዋታውን እዚህ ለመጨረስ እንጫወታለን”‘ ብላለች፡፡ fem-3mars5 –      –       –

የሁለቱ ቡድኖች ዝግጅት

የአልጅጄርያ ብሄራዊ ቡድን ከሰኞ ጀምሮ በአልጀርሽ ስፖርት ሴንተር ዝግጅት ሲያደርግ የቆየ ሲሆን ከቡድኑ ጋር ረጅም ጊዜ ያሳለፉት አሰልጣኝ 26 ተጫዋቾችን በመጥራት ለ5 ቀናት ልምምድ አሰርተዋል፡፡

fem-29-fev2

በአሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው የሚመራው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ከ15 ቀናት በላይ በሱሉልታ እና አአ ስታድየም ዝግጅቱን ሲያደርግ የቆየ ሲሆን አርብ ምሽት 20 ተጫዋቾች ይዞ ወደ አልጀርስ አምርቷል፡፡

image-def0e4ebb2a340fe0ccdd7e5f130ddcf96c0245fcabd3f7efd0ed060b59e1892-V


በአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ማጣርያ አልጄርያ ከ ኢትዮጵያ 12:00 ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡ ሶከር ኢትዮጵያም ከጨዋታው ጋር የተያያዙ መረጃዎችን እዚህ ገፅ ላይ ታቀርብላችኀለች፡፡ መልካም ውሎ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *