ሴካፋ 2021 | ሩዋንዳ ለሴካፋ ውድድር ለተጫዋቾቿ ጥሪ አቅርባለች

በዚህ ሳምንት አዲስ አሠልጣኝ ያገኘው የሩዋንዳ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ለሴካፋ ውድድር ለ35 ተጫዋቾች ጥሪ አቅርቧል።

ከሳምንት በኋላ በባህር ዳር ከተማ በሚጀመረው የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ላይ የሚካፈሉ ብሔራዊ ቡድኖች ለተጫዋቾቻቸው ጥሪ እያቀረቡ ዝግጅት ማድረግ ጀምረዋል። በዛሬው ዕለት በተሰማ መረጃ ደግሞ ከቀናት በፊት የቀድሞውን የራዮን ስፖርት ጊዜያዊ አሠልጣኝ ሶስቴን ሀቢማናን የ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሠልጣኝ አድርጋ የሾመችው ሩዋንዳ ለውድድሩ የሚሆኗትን 35 ተጫዋቾች በዛሬው ዕለት ጠርታለች። የሴካፋ ህግ በሚፈቅደው መሠረት ከ23 ዓመት በታች ተጫዋቾችን አብዝቶ የጠራው አሠልጣኙም ሦስት ከ23 ዓመት በላይ የሆኑ ተጫዋቾችን የማካተት መብት ስላለው ሙሲንዚ አንጌ፣ ኒዮንዚማ ኦሊቨር እና ሙጉንጋ ይቬስ በስብስቡ አካተዋል። ዛሬ ጥሪ የቀረበላቸው ተጫዋቾች እሁድ በሂል ቶፕ ሆቴል እንዲሰባሰቡ ተደርጎ ልምምዳቸውን በፒስ ስታዲየም እንደሚጀምሩ ተጠቁሟል። ጥሩ የተደረገላቸው ተጫዋቾች የሚከተሉት ናቸው :-

ግብ ጠባቂዎች

ንታዋሪ ፊያክሬ (ማሪን)፣ ሀኪዚማና አዶልፍ (ራዮን)፣ ኢሺምዌ ዣንፔር (ኤፒአር)፣ ትዋጊራይዙ አማኒ (ቡጌሴራ)

ተከላካዮች

ኒዪጌና ክሌመንት (ራዮን)፣ በርጌያ ፕሪንስ (ኤፒአር)፣ ርዋቡሂሂ ፕሌሲዴ (ኤፒአር)፣ ንዳዪሺሚዬ ቲዬሪ (ማሪን)፣ ሙኬንጌሬ ክሪስትያን (ቡጌሴራ)፣ ሙስቲንዚ አንጌ (ኤፒአር)፣ ኢሺሙዌ ክሪስቲያን (ኤኤስ ኪጋሊ)፣ ንዳዪሺሚዬ ዲዮዶኔ (ኤፒአር)፣ ሀኪዚማና ፌሊሲዬን (ማሪን)፣ ንሺሚዪማና ኢማኑኤል (ጎሪላ)

አማካዮች

ሩቦኔካ ዦን ቦስኮ (ኤፒአር)፣ ሙጊሻ ቦንሄር (ሙኩራ)፣ ንቲሩሽዋ አይሜ (ፖሊስ)፣ ኒዮንዚማ ኦሊቨር (ኤፒአር)፣ ሚትሲንዶ ይቬስ (ቻርሌሮይ)፣ ኢሺመዌ ሳሌህ (ኪዪቩ)፣ ማኒሺምዌ ጃቤል (ኤፒአር)፣ ኢሺምዌ አኒሴት (ኤፒአር)፣ ሳሙኤል ጉዌሌቴ (ሎቭሬ/ዬልጅየም)

አጥቂዎች

ንሳንዚምፉራ ኬዲ (ኤፒአር)፣ ንዪሪኪንዲ ሳሌህ (ኪዩኩ)፣ በዪሪንጊሮ ላጉ (ኤፒአር)፣ ሩጋንግዚ ፕሮስፐር (ጋሶጊ ዩናይትድ)፣ ኢራጉሀ ሀጂ (ሩትሲሮ)፣ ኒዪቢዚ ራማዳን (ኢቲንሴሌ)፣ ቢራማሂሬ አቤዲ (ኪጋሊ)፣ ሙጉንጋ ይቬስ (ኤፒአር)፣ ቢዚማና ያኒክ (ኤፒአር)፣ ሩዳሲንግዋ ፕሪንስ (ራዮን)፣ ንሹቲ ኢኖሰንት (ኤፒአር)፣ ሲማ ሞሳ (አልተጠቀሰም)