ወላይታ ድቻ ከአንድ ተጫዋች ጋር ተለያይቷል

ወላይታ ድቻ ከአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ጋር በስምምነት መለያየቱ ታውቋል።

ተመስገን ታምራት ከክለቡ ጋር የተለያየ ተጫዋች ነው። ከሀዋሳ ወጣት ቡድን የተገኘውና በተሰረዘው የውድድር ዓመት ወደ ወላይታ ድቻ አምርቶ የነበረው ተመስገን ቀሪ የአንድ ዓመት ውል እየቀረው በስምምነት ከክለቡ ጋር መለያየቱን ለማረጋገጥ ችለናል፡፡

ተጫዋቹ በቀጣይ ወደ አንድ የፕሪምየር ሊግ ክለብ ለማምራት ከጫፍ መድረሱንም ጭምር ሰምተናል፡፡