ከ17 ዓመት በታች ውድድር | በተጓደሉ ቡድኖች ምክንያት አዲስ የምድብ ድልድል ይፋ ሆኗል

በባቱ ከተማ ዛሬ በይፋ የተጀመረው ከ17 ዓመት በታች ውድድር ላይ በተጓደሉት ክለቦች ምክንያት አዲስ የምድብ ድልድል መውጣቱ ታውቋል።

በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት ለመጀመርያ ጊዜ የተዘጋጀው የፕሪምየር ሊግ እና የክልል ከከተሞች የሚሳተፉበት ውድድር በአስራ ስድስት ቡድኖች መካከል በዛሬው ዕለት በባቱ ከተማ መካሄድ ጀምሯል። አስቀድሞ 20 ቡድኖች በአምስት ምድብ ተከፍለው ውድድራቸውን ያደርጋሉ ተብሎ ይፋ ሆኖ መቆየቱ ይታወሳል። ሆኖም ቤኒሻንጉል፣ አፋር፣ አማራ እና ሰበታ ከተማ በውድድሩ ላይ እንደማይሳተፉ ታውቋል። በዚህም መሠረት የምድብ ሀ እና ሐ ሙሉ ቡድኖቹ በመሆናቸው የእነርሱ ምድብ ሳይነካ በቀሪዎቹ በምድብ ለ እና መ ላይ በተጓደሉት ምትክ ማሸጋሸግ እንደሚገባ አወዳዳሪው አካል ባሳለፍነው ዓርብ መወሰኑን ገልፀን ነበር።

ዛሬ ከ10 ጀምሮ ተሳታፊ ክለቦች በተገኙበት የተወሰኑ ውውይቶች ከተካሄዱ በኃላ የዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓቱ ሊወጣ ችሏል። በዚህም መሠረት የውድድሩ አጠቃላይ ድልድል ይሄን ይመስላል።

ምድብ ሀ
አዳማ ከተማ
ኦሮሚያ ክልል
አዲስ አበባ ከተማ
ጋምቤላ ክልል

ምድብ ለ
ወልቂጤ ከተማ
ኢትዮጵያ ቡና
ባህር ዳር ከተማ
ደቡብ ክልል

ምድብ ሐ
ሲዳማ ክልል
ቅዱስ ጊዮርጊስ
ሶማሌ ክልል
ወላይታ ድቻ

ምድብ መ
ሀዋሳ ከተማ
ድሬዳዋ ከተማ
ሐረር ክልል
አርባምንጭ ከተማ

ሰኞ ነሐሴ 17 ቀን ጨዋታዎች

03:00 | ወልቂጤ ከተማ ከ ደቡብ ክልል
05:00 | ኢትዮጵያ ቡና ከ ባህር ዳር ከተማ
07:00 | ሲዳማ ክልለ ከ ወላይታ ድቻ
09:00 | ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ሱማሌ ክልል
(ባቱ ሜዳ)

03:00 | ሀዋሳ ከተማ ከ አርባምንጭ ከተማ
05:00 | ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከ ሐረር ክልል
(በሼር ሜዳ)