የዋልያዎቹ አሰላለፍ ታውቋል

ከሰዓታት በኋላ ከዚምባቡዌ ብሔራዊ ቡድን ጋር የሚጫወተው የዋልያው የመጀመሪያ አሰላለፍ ታውቋል።

ኳታር ለምታስተናግደው የዓለም ዋንጫ ለማለፍ የምድብ የማጣሪያ ጨዋታውን የሚያደርገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ 10 ሰዓት ላይ የዚምባቡዌ አቻውን በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ያስተናግዳል። የቡድኑ ዋና አሠልጣኝ ውበቱ አባተም በጋና አንድ ለምንም ከተረቱበት ጨዋታ ተክለማርያም ሻንቆን በፋሲል ገብረሚካኤል እንዲሁም ታፈሰ ሰለሞንን በመስዑድ መሐመድ ለውጠው ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ታውቋል።

አሠልጣኙ በጨዋታው የሚጠቀሙትን የመጀመሪያ አሰላለፍም የሚከተለው ነው።

ግብ ጠባቂ

ፋሲል ገብረሚካኤል

ተከላካዮች

አሥራት ቱንጆ
ያሬድ ባየህ
አስቻለው ታመነ
ረመዳን የሱፍ

አማካዮች

ይሁን እንደሻው
መስዑድ መሐመድ
ሽመልስ በቀለ

አጥቂዎች

አቡበከር ናስር
ጌታነህ ከበደ
አማኑኤል ገብረሚካኤል