ፈጣኑ የመስመር አጥቂ ለሀድያ ሆሳዕና ፈረመ

ሀድያ ሆሳዕና የመስመር አጥቂውን በአንድ ዓመት ውል ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል፡፡

በአዲሱ አሰልጣኙ ሙሉጌታ ምህረት እና ረዳቶቹ መሪነት ከሳምንታቶች በፊት በመቀመጫው ሆሳዕና ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን የጀመረው ሀድያ ሆሳዕና በሲዳማ ጎፈሬ ዋንጫ ላይ ለመካፈል ከአንድ ቀን በፊት ወደ ሀዋሳ በመምጣት በሴንትራል ሆቴል ማረፊያውን በማድረግ በርከት ያሉ አዳዲስ ፈራሚዎችን ከነባሮቹ ጋር በማቀናጀት ልምምዱን የቀጠለ ሲሆን አሁን ደግሞ ፈጣኑን የመስመር አጥቂ አስቻለው ግርማን በይፋ በአንድ ዓመት ውል የግሉ አድርጓል፡፡

የቀድሞው የሱሉልታ ከተማ ፣ ኢትዮጵያ ቡና ፣ ሀዋሳ ከተማ ፣ ጅማ አባጅፋር ፣ ሰበታ ከተማ እና እንዲሁም የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን በድሬዳዋ ከተማ ያሳለፈው ይህ የመስመር አጥቂ በይፋ የአሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረቱን ክለብ ተቀላቅሏል፡፡