ቻምፒየንስ ሊግ፡ በምስራቅ አፍሪካ ደርቢ ያንጋ አፍሪካ ኤፒአርን አሸንፏል

የ2016 ኦሬንጅ ካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ ተደርገዋል፡፡ የኢትዮጵያው ተወካይ ቅዱስ ጊዮርጊስ የ2015 የቻምፒየንስ ሊጉን አሸናፊ ቲፒ ማዜምቤን ገጥሞ 2 አቻ ተለያይቷል፡፡ በምስራቅ አፍሪካ ደርቢ የታንዛኒያው ያንጋ አፍሪካ የሩዋንዳውን ኤፒአርን ከሜዳው ውጪ 2-1 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ተስፋውን አለምልሟል፡፡ የግብፁ ሃያል ክለብ አል አሃሊ ከሜዳው ውጪ ከአንጎላው ሪክሬቲቮ ዱ ሊቦሎ ጋር ተጫውቶ 0-0 ወጥቷል፡፡ የ2015 የቻምፒየንስ ሊጉ የፍፃሜ ግማሽ ተፋላሚ የሱዳኑ አል ሂላል በሊቢያው አል አሃሊ ትሪፖሊ ያልተጠበቀ ሽንፈትን ቀምሷል፡፡
ኪጋሊ ላይ በተደረገ ጨዋታ ያንጋ አፍሪካ በጁማ አብዱል እና ታባን ካሙሶኮ ግቦች ታግዞ የሩዋንዳ የጦሩ ቡድን የሆነውን ኤፒአርን አሸንፏል፡፡ ለኤፒአር ፓትሪክ ሲቦማና አንድ ግብ ማስቆጠር ችሏል፡፡ ማርቲን ዮል በመጀመሪያ የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታቸው ክለባቸው አል አሃሊ ከሪክሬቲቮ ዱ ሊቦሎ ያለግ አቻ መውጣት ችሏል፡፡ የሞሮኮው ዋይዳድ ካዛብላንካ የማዳጋስካሩን ሲኤንኤፒኤስ 5-1 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል፡፡ የሱዳኑ አል ሂላል ከሜዳው ውጪ በአል አሃሊ ትሪፖሊ 1-0 ተሸንፏል፡፡ ሌላው የሱዳን ክለብ ኤል ሜሪክ ከሜዳው ውጪ የናይጄሪያውን ዋሪ ዎልቭስን 1-0 ማሸነፍ ችሏል፡፡
የደቡብ አፍሪካው ካይዘር ቼፍስ ጆሃንስበርግ በሚገኘው ኤፍኤንቢ ስታዲየም (ሶከር ሲቲ ስታዲየም) በኮትዲቯሩ ታላቅ ክለብ አሴክ ሚሞሳ 1-0 ተሸንፏል፡፡ የአሴክ ሚሞሳን የድል ግብ አዳማ ባካ ዮኮ በግንባር በመግጨት አስቆጥሯል፡፡ ዛማሌክ የካሜሮኑን ዩኒየን ዱዋላ በብርኪናፋሶው ተከላካይ መሃመድ ኮፊ ግብ ከሜዳው ውጪ 1-0 አሸንፏል፡፡

Image.ashx
የቻምፒየንስ ሊጉ መልስ ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ የሚደረጉ ይሆናል፡፡

የመጀመሪያ ዙር ውጤቶች

ቅዱስ ጊዮርጊስ (ኢትዮጵያ) 2-2 ቲፒ ማዜምቤ (ዲ.ሪ. ኮንጎ)
ማሜሎዲ ሰንዳውንስ (ደቡብ አፍሪካ) 2-0 ኤሲ ሊዮፖርድስ (ኮንጎ ብራዛቪል)
ስታደ ማሊያን (ማሊ) 2-0 ኮተን ስፖርት (ካሜሮን)
ዜስኮ ዩናይትድ (ዛምቢያ) 4-1 ሆሮያ (ጊኒ)
ኤፒአር (ሩዋንዳ) 1-2 ያንጋ አፍሪካ (ታንዛኒያ)
ካይዘር ቼፍስ (ደቡብ አፍሪካ) 0-1 አሴክ ሚሞሳ (ኮትዲቯር)
ክለብ አፍሪካ (ቱኒዚያ) 1-0 ኤምኦ ቤጃ (አልጄሪያ)
ዋይዳድ ካዛብላንካ (ሞሮኮ) 5-1 ሲኤንኤፒኤስ (ማዳጋስካር)
አል አሃሊ ትሪፖሊ (ሊቢያ) 1-0 አል ሂላል (ሱዳን)
ሬክሬቲቮ ዱ ሊቦሎ (አንጎላ) 0-0 አል አሃሊ (ግብፅ)
ኤስ ቪታ (ዲ.ሪ. ኮንጎ) 1-0 ፌሮቫያሮ (ሞዛምቢክ)
ዋሪ ዎልቭስ (ናይጂሪያ) 0-1 ኤል ሜሪክ (ሱዳን)
ኤቷል ዲ ኮንጎ (ኮንጎ ብራዛቪል) 1-1 ኢኤስ ሴቲፍ (አልጄሪያ)
ኤኒየምባ (ናይጄሪያ) 5-1 ቪታሎ (ቡሩንዲ)
ዩኒየን ዱዋላ (ካሜሮን) 0-1 ዛማሌክ (ግብፅ)
ኦሲ ኮሪብጋ (ሞሮኮ) 1-1 ኤቷል ደ ሳህል (ቱኒዚያ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *