የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሊግ ቀጣይ ጨዋታዎች በዚህ ሳምንት ተደርገዋል፡፡ 4 ዞኖች በዚህ ሳምንት እረፍት ያደረጉ ሲሆን 3 ዞኖች ጨዋታወቸውን አድርገዋል፡፡ የሰሜን ዞን ሀ በዚህ ሳምንት እረፍት እንደሚያደርግ ፕሮግራም ወጥቶለት የነበረ ቢሆንም ባለፈው ሳምንት ሳይካሄድ በመቅረቱ ክለቦቹ በዚህ ሳምንት ጨዋታ አድርገዋል፡፡
-ዞኖቹ እረፍት የሚያደርጉበት ምክንያት
ዞኖቹ በውስጣቸው የያዟቸው ክለቦች ብዛት እኩል ባለመሆኑ ውድድሩ በተመሳሳይ ወቅት እንዲጠናቀቅ በማሰብ የክለቦቹ ቁጥር አነስተኛ የሆኑት ዞኖች በመሃል በመሃል እረፍት እያደረጉ ውድድሩን ይቀጥላሉ፡፡
የዚህ ሳምንት ጨዋታዎች ውጤቶች የሚከተሉት ናቸው
መካከለኛ ዞን ሀ (6ኛ ሳምንት)
እሁድ መጋቢት 4 ቀን 2008
ለገጣፎ ከተማ 1-1 ቱሉ ቦሎ ከተማ
ቡታጅራ ከተማ 2-0 ዱከም ከተማ
ሰኞ መጋቢት 5 ቀን 2006
ልደታ ክፍለ ከተማ 1-1 ቦሌ ክፍለ ከተማ
ማክሰኞ መጋቢት 6 ቀን 2008
09፡00 – ንፋስ ስልክ ላፍቶ ከ መቂ ከተማ (አበበ ቢቂላ)
ሰሜን ዞን ሀ (5ኛ ሳምንት)
እሁድ መጋቢት 4 ቀን 2008
ዳባት ከተማ 1-0 አምባ ጊዮርጊስ
አዊ አምፒልታቅ 1-0 ደባርቅ
አማራ ፖሊስ 1-1 ዳሞት ከተማ
ደቡብ ዞን ለ (6ኛ ሳምንት)
እሁድ መጋቢት 4 ቀን 2008
አንበሪቾ 1-0 ጎፉ ባሪንቼ
ሮቤ ከተማ 0-0 ጎባ ከተማ
ዲላ ከተማ 2-1 ኮንሶ ኒውዮርክ
ጋርዱላ 1-0 ወላይታ ሶዶ
-በዚህ ሳምንት ጨዋታ ያልተደረገባቸው ዞኖች
ሰሜን ዞን ለ ፣ መካከለኛ ዞን ለ ፣ ደቡብ ዞን ሀ እና ምስራቅ ዞን