አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች | ሀዲያ ሆሳዕና ከ ባህር ዳር ከተማ

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በቀጣይነት ስለሚያስተናግደው ጨዋታ የመጨረሻ መረጃዎችን አጠናቅረናል።

ሀዲያ ሆሳዕና ከፋሲሉ ጨዋታ ጋር ሲተያይ ባደረገው ብቸኛ ለውጥ በመስመር አጥቂነት ዑመድ ዑኩሪን በፀጋዬ ብርሀኑ የተካበት ብቻ ሆኗል። ባህር ዳር ከተማ በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ካሳካው ድል ሦስት የአሰላለፍ ለውጥ አድርጓል። በዚህም መናፍ ዐወል፣ ፍቅረሚካኤል ዓለሙ እና አህመድ ረሺድ በመሳይ አገኘሁ ፣ ዜናው ፈረደ እና ተመስገን ደረሰ ቦታ ጨዋታውን ይጀምራሉ።

የሀዲያ ሆሳዕናው አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምኅረት ከጨዋታው በፊት በሰጡት አስተያየት ካለፈው ጨዋታ የተለየ ነገር እንደሌለ እና ለሁሉም ክለቦች ያደረጉትን ዝግጅት ዛሬም ለመተግበር አስበው እንደመጡ ገልፀው አሁንም አጥቅቶ እና ጥሩ የሚጫወት ቡድንን ማሳየት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።

የባህር ዳር ከተማው አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ በበኩላቸው የመጀመሪያውን ጨዋታ እንደማሸነፋቸው ዛሬም በተሻለ የቡድን መንፈስ ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ገልፀው ሀድያ የባለፈው በፋሲል ሽንፈት ድክመቱን እንደማይገልፀው እና ጠንካራ ተፎካካሪ መሆኑን ገልፀዋል።

የሀድያ ሆሳዕና የጥቅማ ጥቅም ጉዳይ በተወሰነ መልኩ ተፈትቶ ክለቡ ለተጫዋቾቹ የገባውን ገንዘብ የፈፀመ ሲሆን ዛሬ የክለቡ የበላይ አካላት እና ተጫዋቾች በሀዋሳ ሴንትራል ሆቴል ባደረጉት ውይይት ሙሉ በሙሉ ክለቡ ለተጫዋቾቹ የገባውን ቃል በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመፈፀም እንዳቀደ እና በቀጣይም ችግሩን ከስር መሠረቱ እንደሚፈታ አመራሩ ገልፀው ስብሰባው ተጠናቋል፡፡

ጨዋታውን ፌደራል ዳኛ አሸብር ሰቦቃ በመሀል ዳኝነት ይመሩታል።

ሁለቱ ተጋጣሚዎች ዛሬ ይዘው የሚገቡት አሰላለፍ ይህንን ይመስላል።

ሀዲያ ሆሳዕና

30 መሳይ አያኖ
12 ብርሀኑ በቀለ
16 ፍሬዘር ካሳ
6 ኤሊያስ አታሮ
14 እያሱ ታምሩ
21 ተስፋዬ አለባቸው
8 ሳምሶን ጥላሁን
10 ፍቅረየሱስ ተወልደብርሀን
25 ሀብታሙ ታደሰ
31 ዑመድ ዑኩሪ
9 ባዬ ገዛኸኝ

ባህር ዳር ከተማ

44 ፋሲል ገብረሚካኤል
13 አህመድ ረሺድ
6 መናፍ ዐወል
15 ሰለሞን ወዴሳ
2 ፈቱዲን ጀማል
7 ግርማ ዲሳሳ
21 ፍቅረሚካኤል ዓለሙ
25 አለልኝ አዘነ
10 ፉዓድ ፈረጃ
14 ፍፁም ዓለሙ
77 ኦሴ ማዉሊ