ቅዱስ ጊዮርጊስ ሆላንዳዊ አሰልጣኝ ቀጠረ

 

ቅዱስ ጊዮርጊስ ማርቲን ኩፕማን የተባሉ ሆላንዳዊ አሰልጣኝ መቅጠሩን ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡ ባለፈው ወር ብራዚላዊውን አሰልጣኝ ኔይደር ዶ ሳንቶስ ከኃላፊነት ያሰናበተው ቅዱስ ጊዮርጊስ የ59 አመቱ ሆላንዳዊ ማርቲን ኩፕማንን አዲስ አሰልጣኝ አደርጎ ቀጥሯል፡፡

የቀድሞው የትዎንቴ አማካይ ኩፐር ከ90ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ በሆላንድ ፣ ግሪክ ፣ ሳኡዲ አረብያ እና ጋና የማሰልጠን ልምድ ያላቸው ሲሆን ከጁላይ 1 ጀምሮ ማለትም የዚህ የውድድር ዘመን እንደተጠናቀቀ ስራቸውን በይፋ ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከዚህ በፊት ሆላንዳውያኑ ሃንስ ቫንደር ፕሊዩም በ1996 ፣ ማርት ኑይ በ2006 እና ሬኔ ፌለር 2006 በቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኝነት አልፈዋል፡፡

ፎቶ - St George
ፎቶ – St George

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *