የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተከላካይ ዋሊድ አታ የስዊድኑን ቢኬ-ሃከንን ለቅቆ የቱርኩ ጌንክልብርጊ ክለብ ተቀላቅሏል፡፡
የ28 አመቱ ተከላካይ ባለፈው ክረምት ከሌላው የስቂድን ክለብ ሂልስንግቦርግ ወደ ቢኬ ሃከን ከተዛወረ በኋላ በ26 ጨዋዎች ላይ ቢጫ እና ጥቁሩን መለያ ለብሶ ተጫውቷል፡፡
የቢኬ – ሃከን ሃላፊ ካርልሰን ስለ ዝውውሩ ጉዳይ በሰጡት አስተያየት የኮንትራት አስገዳጅነት ዋሊድን እንዲለቁ እንዳደረጋቸው ተናግረዋል፡፡ ‹‹ ዋሊድ ለቢኬ-ሃከን ሲፈርም በሌሎች ሃገራት የተሻለ ክለብ ካገኘ ልንለቀው እንደምንችል በኮንትራቱ ላይ ተስማምተናል፡፡ የሱ መልቀቅ በተከላካይ ክፍላችን ላይ ክፍተት ቢፈጥርም በቶሎ ችግራችንን ለመፍተት ጥረት እናደርጋለን፡፡ ወደፊት ለሚገጥመው የእግርኳስ ህይወት መልካሙን እንመኝለታለን›› ብለዋል፡፡
ዋሊድ የተቀላቀለበት ክለብ በአሁኑ ሰአት በቱርክ ሱፐር ሊግ 8ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
