የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 19ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ በተካሄዱ 2 ጨዋታዎች ተጠናቋል፡፡
ሶዶ ላይ ሀዋሳ ከነማን ያስተናገደው ወላይታ ድቻ 1-0 አሸንፏል፡፡ የወላይታ ድቻን የድል ግብ ከመረብ ያሳረፈው አጥቂው አላዛር ፋሲካ ነው፡፡ ወላይታ ድቻ የዛሬው ድሉ ከ4 ተከታታይ ጨዋታዎች ሽንፈት በኋላ የመጀመርያ ድል ሆኖ ተመዝግቦለታል፡፡
አዲስ አበባ ስታድየም ላይ በወራጅ ስጋት ውስጥ የሚገኘው ኤለክትሪክ በሊጉ ግርጌ ላይ የሚገኘው ወልድያን አስተናግዶ 2-0 አሸንፏል፡፡ የቀዮቹን የድል ግቦች ፒተር ኑዋድኬ እና ፍቅረየሱስ ተክለብርሃን ከመረብ አሳርፈዋል፡፡ ኤሌክትሪክ ከድሉ በኋላ የነጥብ ድምሩን 21 አድርሶ 10ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ወልድያ በ9 ነጥቦች የመጨረሻውን ደረጃ ይዟል፡፡