ወርሀዊ የፊፋ የሀገራት ደረጃ ዛሬ ወጥቷል

የዓለም የእግርኳስ የበላይ አካል የሆነው ፊፋ በየወሩ የአባል ሀገራቱን ወርሃዊ ደረጃ ይፋ እንደሚያደርግ ይታወቃል። ዛሬ ደግሞ ያሳለፍነውን ወር የአባል ሀገራቱን ደረጃ ይፋ ሲያደርግ የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን ያለ ምንም ለውጣ ባለበት 137ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ካሳለፍነው ወር 8.52 ነጥቦችን በማሻሻል 1087.89 ነጥቦችን ቢያገኝም የደረጃ ማሻሻል እና መውረድ ሳያያሳይ ባለበት ደረጃ ተቀምጧል። ዋልያው ከዓለም 137ኛ ደረጃ ላይ ቢቀመጥም ከአፍሪካ ካሉ አቻዎቹ በ39ኙ ተበልጦ 40ኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ ተገዷል።

ላለፉት በርካታ ጊዜያት የዓለም ቁንጮ የነበረችው ቤልጂየም አሁንም በመሪነቷ ስትቀጥል ብራዚል እና ፈረንሳይ ተከታዮቹን ቦታዎች ይዘዋል። የአህጉራችን አፍሪካን ደረጃ ደግሞ ሴኔጋል ስትመራው ሞሮኮ እንዲሁም ቱኒዚያ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።