አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች | ፋሲል ከነማ ከ አርባምንጭ ከተማ

ከደቂቃዎች በኋላ በሚጀምረው ጨዋታ ዙሪያ የመጨረሻ ነጥቦችን እነሆ !

ፋሲል ከነማ የመጀመሪያ ሽንፈት ከቀመሰበት የአዲስ አበባ ከተማው ጨዋታ ሁለት ለውጦችን ሲያደርግ በግል ጉዳይ ያልነበረው ሽመክት ጉግሳ እና ዓለምብርሀን ይግዛው በናትናኤል ገብረጊዮርጊስ እና ሰዒድ ሀሰን ምትክ ወደ ሜዳ ይገባሉ።

ተደጋጋሚ ድሎችን እያሳካ በሚገኘው አርባምንጭ ከተማ በኩል ግን ተካልኝ ደጀኔ በመላኩ ኤሊያስ ከመተካቱ በቀር ቀሪው አሰላለፍ ከባህር ዳሩ ድል የተለየ አይደለም።

ጨዋታውን ኢንተርናሽናል ዳኛ ቴዎድሮስ ምትኩ በመሀል ዳኝነት ይመሩታል።

የሁለቱ ቡድኖች የዛሬው የመጀመሪያ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል

ፋሲል ከነማ

1 ሚኬል ሳማኬ
27 ዓለምብርሀን ይግዛው
5 ከድር ኩሊባሊ
16 ያሬድ ባዬ
21 አምሳሉ ጥላሁን
8 ይሁን እንደሻው
14 ሀብታሙ ተከስተ
17 በዛብህ መለዮ
7 በረከት ደስታ
19 ሽመክት ጉግሳ
9 ፍቃዱ ዓለሙ

አርባምንጭ ከተማ

1 ሳምሶን አሰፋ
14 ወርቅይታደሰ አበበ
15 በርናርድ ኦቼንግ
4 አሸናፊ ፊዳ
3 መላኩ ኤሊያስ
20 እንዳልካቸው መስፍን
21 አንዱአለም አስናቀ
23 ሀቢብ ከማል
22 ፀጋዬ አበራ
26 ኤሪክ ካፒያቶ
9 በላይ ገዛኸኝ