በአንደኛ ሊግ በክፍያ ምክንያት በምድብ ሳይካተቱ የነበሩ ክለቦች በዛሬው ዕለት ተደልድለዋል

በኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ በክፍያ ምክንያት የምድብ ድልድሉ ላይ ሳይካተቱ ቀርተው የነበሩ ክለቦች የተጠየቁትን መስፈርት በማሟላታቸው በዛሬው ዕለት ሊደለደሉ ችለዋል፡፡

የ2014 የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ የምድብ ድልድል ከቀናት በፊት መውጣቱ ይታወሳል፡፡ በወቅቱ ክለቦች የሚጠበቅባቸውን የምዝገባ፣ የዳኞች እና ኮሚሽነሮች ክፍያ የከፈሉ ክለቦች በምድብ ሲደለደሉ ስምንት ክለቦች ግን ክፍያቸውን ሳይፈፅሙ በመቅረታቸው በዕጣው ተሳታፊ መሆን ሳይችሉ ቀርተው እንደነበር ይታወሳል፡፡ በትናንትናው ዕለት ስምንቱ ክለቦች የተጠየቁትን ክፍያ ተፈፃሚ በማድጋቸው በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የመሰብሰቢያ አዳራሽ የፌዴሬሽኑ የውድድር ዳይሬክተር አቶ ከበደ ወርቁ እና የአንደኛ ሊግ ኮሚቴዎች በተገኙበት የዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓቱ መከናኑን ፌዴሬሽኑ ገልፀዋል፡፡

በዚህም መሠረት የቀሩት ክለቦች በሚከተለው መልኩ ተደልድለዋል፡፡

ልደታ ክፍለ ከተማ እና ሊሙ ገነት – ምድብ ሀ

ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፣ ቫርኔሮ ወረዳ 13 እና ጂንካ ከተማ – ምድብ ለ

ሱሉልታ ከተማ ፣ ቢሸፍቱ ከተማ እና ሮቤ ከተማ – ምድብ ሐ