ድሬዳዋ ከተማ ለአሠልጣኙ ጥሪ አቅርቧል

ድሬዳዋ ከተማ አሠልጣኙ ወደ ክለቡ መቀመጫ ከተማ አምርተው ሪፖርት እንዲያቀርቡ ጥሪ አስተላልፏል።

\"\"

ባሳለፍነው ክረምት ዮርዳኖስ ዓባይን ዋና አሠልጣኝ አድርጎ የሾመው ድሬዳዋ ከተማ በ2015 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 17 ጨዋታዎች 21 ነጥቦችን በመያዝ 12ኛ ደረጃ ላይ እንደተቀመጠ ይታወቃል። ካለፉት ስድስት ጨዋታዎች አንዱን ብቻ የረታው ክለቡ የውጤት መሻሻል እንዲመጣ ከአሠልጣኙ ጋር ውይይት እንዳደረገ እና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያዎች እንደተሰጡ ሲሰማ የነበረ ሲሆን በትናንትናው ዕለት ደግሞ በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ በሚገኘው ለገጣፎ ለገዳዲ 2ለ1 ተሸንፏል።

\"\"

ይህ ወቅታዊው ውጤት ያላስደሰተው የክለቡ አመራርም አሠልጣኝ ዮርዳኖስ ዓባይ ወደ ድሬዳዋ ተጉዘው ሪፖርት እንዲያቀርቡ ጥሪ አስተላልፏል። አሠልጣኙም ወደ ስፍራው አምርተው ሪፖርት አድርገው ቀጣይ ውሳኔዎች እንደሚወሰኑ ሰምተናል።