መቻል ተከላካይ አስፈርሟል

በዛሬው ዕለት አዳዲስ ተጫዋቾችን ማስፈረም የጀመሩት መቻሎች አስቻለው ታመነን የግላቸው አድርገዋል።

በአሠልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ የሚመሩት መቻሎች የሦስት ነባር ተጫዋቾቻቸውን ውል ማራዘማቸውን እና ነስረዲን ኃይሉን እንዲሁም አቤል ነጋሽን ወደ ስብስባቸው መቀላቀላቸውን መዘገባችን ይታወሳል። ሶከር ኢትዮጵያ አሁን ባገኘችው መረጃ መሠረት ደግሞ የመሐል ተከላካዩ አስቻለው ታመነ የክለቡ ሦስተኛ ፈራሚ ሆኗል።

የቀድሞ የደደቢት እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋች የነበረው አስቻለው ያለፉትን ሁለት ዓመታት በፋሲል ከነማ ያሳለፈ ሲሆን አሁን በሁለት ዓመት ውል መቻልን በይፋ ተቀላቅሏል።