ቸርነት ጉግሳ በይፋ ባህር ዳር ከተማን ተቀላቅሏል

ባህር ዳር ከተማን ለመቀላቀል ስምምነት ላይ ደርሶ የነበረው ተጫዋች ከደቂቃዎች በፊት ክለቡን በይፋ ተቀላቅሏል።

በአሠልጣኝ ደግአረገ ይግዛው የሚመራው ባህር ዳር ከተማ ከፊቱ ላለበት የካፍ ኮንፌዴሬሽን ካፕ የማጣሪያ ጨዋታ እና የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም ዝግጅት ላይ የሚገኝ ሲሆን ከሳምንታት በፊት ወደ ቡድኑ ለመቀላቀል ስምምነት ላይ ደርሶ የነበረውን ቸርነት ጉግሳንም ከደቂቃዎች በፊት በይፋ ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።

የወላይታ ድቻን ወጣት እና ዋናውን ቡድን ማገልገል የቻለው ቸርነት ከአምስት ዓመታት የክለቡ ቆይታ በኋላ በቅዱስ ጊዮርጊስ ያለፉትን ሁለት ዓመታት በመጫወት ከክለቡ ጋር የሊጉን ዋንጫ ማንሳቱ አይዘነጋም። ተጫዋቹ ከፈረሰኞቹ ጋር ያለው ውል ከተቋጨ በኋላም ዛሬ አመሻሽ በይፋ ባህር ዳር ከተማን በሁለት ዓመት ውል ተቀላቅሏል።