የአሰልጣኞች አስተያየት | ሀድያ ሆሳዕና 2-4 ጅማ አባ ጅፋር

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

የ11ኛው ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታ ጅማ አባ ጅፋር ሀድያ ሆሳዕናን 4-2 በሆነ ውጤት ከረታ በኋላ ሁለቱም አሰልጣኞች ስለ ጨዋታው ተከታዩን ብለዋል።

አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ – ጅማ አባ ጅፋር

ስለ ድሉ

“ቅድም መግቢያዬ ላይ እንደተናገርኩት ይሄ ጨዋታ በታክቲካል ዲሲፕሊን የታጠረ ነው፡፡’ ጠንካራ ጎናቸው ሀድያ ምንድ ነው ?’ ያቺን ደግሞ ማቆም ነበር፡፡ ባሰብነው መልኩ ስለሄዱልን ዘጠናውን ደቂቃ በዚህ መልኩ ውጤታማ ሆነናል፡፡

የድሬዳዋ ተከታታይ ድል

“እውነት ነው ፤ መግቢዬ ላይ ብዬ ነበር፡፡ ያንን እያየን ነው፡ የበለጠ ውጤታማ የምንሆነው። ደግሞ በሂደት የምናስመዘግበው ውጤት የተሻለ ነገር ይሰጠናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።

ተከታታይ ድሉ ስለሚያመጣው ተነሳሽነት

“እጅግ በጣም ተነሳሽነት ይኖረዋል፡፡እንደሚታወቀው ቡድኔ ተከታታይ ነጥብ ነው የጣለው። ይሄን እኔም ተመልካችም የጠበቀው ነገር አይደለም። በቀጣይ ጨዋታ ላይ የተሻለ ተነሳሽነት ፈጥሮ ውጤታማ ያደርግልናል ብዬ አስባለው፡፡”

አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት – ሀድያ ሆሳዕና

ስለ ውጤቱ

“እንደተመለከታችሁት ነው። ያው አራት ለሁለት ተሸንፈናል ምንም ማድረግ አይቻልም። ብዙ ጥረናል ግን ያው ጥቃቅን ስህተቶች ነበሩብን እነሱ በእርሱ ተጠቅመዋል፡፡

እንደ ግለሰብ የሚታዩ ስህተቶች

“አዎ ይሄ እግርኳስ ነው፡፡ እንደ ቡድንም እንደ ግለሰብም ስህተቶች ቢኖሩም እኔ ግን እንደ ቡድን ነው የምመለከተው። ስንሸነፍ ሁላችንም ነው የምንሸነፈው እግር ኳስ ስለሆነ ደግሞ ፔናሊቲ ተስቷል ይሳታልም። ሌሎች ዓለም ላይም የሚስቱ ስላሉ እግርኳስ ያለ ስህተት ደግሞ ውጤት አይኖርም እና ዛሬ እኛ ብንሳሳትም ተሸንፈናል ለቀጣይ ደግሞ ዕድለኛ የምንሆንበት አጋጣሚ ሊኖር ይችላል እና እንደ ቡድን ተመልክተነው ለቀጣዩ ተዘጋጅተን እንመጣለን፡፡

መሀል ሜዳ ላይ በልጦ ስለመሸነፍ

“እግርኳስ መሀል ላይ ብታሸንፍም ብትበልጥም ዳርም ብትበልጥ ጎል ካላገባህ ያው ተሸንፈህ ትወጣለህ። የሞከርነውም ለዛ ነው እኛ ግን አጋጣሚ ሆኖ ባስብነው መልኩ ጎል ልናስቆጥር አልቻልንም። እነሱ ደግሞ ባገኙት አጋጣሚ አስቆጥረዋል፡፡በዛ ምክንያት እንጂ መሀልም ዳርም ልዩነት የለውም ዋናው ምንድነው ከበለጥክ ማሸነፍ አለብህ። በዚህ መልኩ ነው እኔሞ የማየው።”