ከፍተኛ ሊግ | ሀላባ ከተማ አዲስ አሠልጣኝ ቀጥሯል

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሀ ስር የሚገኘው ሀላባ ከተማ አሰልጣኝ አላምረው መስቀሌን በማሰናበት አዲስ አሠልጣኝ በቦታው ተክቷል፡፡

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የ2014 የውድድር አመትን በአሰልጣኝ አላምረው መስቀሌ እየተመራ በምድብ ሀ በሆሳዕና ከተማ በነበረው የመጀመሪያው ዙር ጨዋታዎች ላይ ተካፋይ የነበረው ሀላባ ከተማ ከዘጠኝ የዙሩ ጨዋታዎች በስምንት ነጥብ 8ኛ ደረጃ ላይ በመቀመጡ የክለቡ የበላይ አካላት ባደረጉት ውይይት አሰልጣኙን ከቦታው በማንሳት በምትኩ አዲስ አሰልጣኝ መርጧል፡፡ ቾንቤ ገብረህይወትም አዲሱ የክለቡ አሰልጣኝ በመሆን ተሹሟል፡፡

ከሀዋሳ ከተማ የታዳጊ ቡድን የጀመረው የአሰልጣኝነት ዘመኑ በመቀጠል በሲዳማ ቡና ረዳት እና ጊዜያዊ አሰልጣኝ እንዲሁም ደግሞ ደቡብ ፖሊስን በዋና አሰልጣኝነት አሰልጥኖ አልፏል፡፡ እስከ አምናው የውድድር ዓመት ድረስ ነቀምቴ ከተማን ለአራት ዓመታት በማሰልጠን ቆይታ የነበረው አሰልጣኙ ሀላባ ከተማን በሁለተኛው ዙር የከፍተኛ ሊግ ጨዋታዎች በዋና አሰልጣኝነት ለመምራት መሾሙን ክለቡ ለሶከር ኢትዮጵያ አሳውቋል፡፡