የፕሪምየር ሊጉ ሁለተኛ ዙር የጅማሮ ቀን ለሦስተኛ ጊዜ ተገፍቷል

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛው ዙር ውድድር የሚጀምርበት ቀን ላይ ማሻሻያ ተደርጓል፡፡

የ2014 ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያው ዙር አስራ አምስት ጨዋታዎች በሀዋሳ እና ድሬዳዋ ተደርገው በአሁኑ ወቅት እረፍት ላይ ይገኛል፡፡ ከአስራ ስድስተኛው ሳምንት እስከ ሠላሳኛው ድረስ የሚደረጉ የሁለተኛው ዙር ጨዋታዎች በአዳማ እና ባህር ዳር እንደሚቀጥሉ በቀደመው ዘገባችን ጠቁመናችሁ ነበር፡፡

የፕሪምየር ሊጉ አወዳዳሪ አካል የሆነው የሊግ ካምፓኒ የሁለተኛውን ዙር ጨዋታ ቀደም ብሎ መጋቢት 4 ይጀመራል ካለ በኋላ ወደ መጋቢት 19 ባልታወቀ ምክንያት መሸጋገሩ የተነገረ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሜዳ በቂ የሆነ ዝግጅት እንዲደረግበት በሚል ለሦስተኛ ጊዜ ቀደም ካለው በሁለት ቀን ተገፍቶ መጋቢት 21 እንዲጀመር ዛሬ ተወስኗል፡፡