ዮሃንስ ሱጌቦ ወደ ኢትዮ ኤሌክትሪክ አምርቷል

ከሀዋሳ ከተማ ታዳጊ እስከ ዋናው ቡድን ድረስ ግልጋሎት የሰጠው ተጫዋች ማረፊያው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሆኗል፡፡

ከከፍተኛ ሊጉ ምድብ ሀ ወደ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ያደገው ኢትዮ ኤሌክትሪክ እስከ አሁን ሰለሞን ደምሴ ፣ ሙሴ ካባላ ፣ ፍቅሩ ወዴሳ፣ ኃይሌ ገብረትንሳይ፣ ጌቱ ኃይለማርያም ፣ ተስፋዬ በቀለ ፣ ታፈሰ ሰርካ እና ወንድማገኝ ማዕረግን ያስፈረመ ሲሆን አሁን ደግሞ ዘጠነኛ ፈራሚውን ሁለገቡ ዮሃንስ ሱጌቦ አድርጓል።

በአሰልጣኝ ተመስገን ዳና ይመራ ከነበረው የሀዋሳ ከተማ ከ17 እና ከ20 ዓመት በታች ቡድኖች ውስጥ ተጫውቶ ያሳለፈው የግራ መስመር ተከላካይ እና የአማካይ ስፍራ ተጫዋች አምስት ዓመታትን የሀዋሳ ዋናውን ቡድን መለያ በመልበስ ቆይታን አድርጎ በቀጣዩ ዓመት በኤሌክትሪክ ለመጫወት ፊርማውን አኑሯል።