ወደ ፕሪምየር ሊጉ ዳግም የመመለስ ዕድል ያገኘው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በአዳማ ከተማ ዝግጅቱን ያከናውናል፡፡
በከፍተኛ ሊጉ ላለፉት አራት ዓመታት ተሳትፎን በማድረግ ወደ ነበረበት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የተመለሰው አንጋፋው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ለቀጣዩ የ2015 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር የአሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተናን ውል እና የነባር ተጫዋቾችን ኮንትራት ከማደስ ጀምሮ ሰለሞን ደምሴ ፣ ሙሴ ካቤላ ፣ ፍቅሩ ወዴሳ፣ ኃይሌ ገብረትንሳይ፣ ጌቱ ኃይለማርያም ፣ ተስፋዬ በቀለ ፣ ታፈሰ ሰርካ ፣ ወንድማገኝ ማዕረግን እና ዮሃንስ ሱጌቦን በአዲስ መልክ ሲቀላቅል ከሰሞኑም ተጨማሪ ተጫዋቾችን እንሚያስፈርምም ይጠበቃል፡፡ ይሁን እና ክለቡ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን መቼ እና የት እንደሚያደርግ ክለቡ ለዝግጅት ክፍላችን መረጃ ልኳል፡፡
በዚህም መሠረት የክለቡ ተጫዋቾች ሐምሌ 28 እስከ ሐምሌ 30 ዕለት ድረስ የህክምና ምርመራን ካደረጉ በኋላ ከሰኞ ነሀሴ 2 – 2015 ጀምሮ በአዳማ ከተማ ላሊ ሆቴል ማረፊያቸውን በማድረግ ዝግጅት እንደሚጀምሩ አረጋግጠናል፡፡