የደቡብ አፍሪካ እና ላይቤሪያ ጨዋታ በኢትዮጵያዊ ዳኞች ይመራል

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ጨዋታ ደቡብ አፍሪካ እና ላይቤሪያ የሚያደርጉት ፍልሚያ በሀገራችን ዳኞች ይመራል።

\"\"

አይቮሪኮስት ለምታስተናግደው የ2023 አፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የአህጉራችን ብሔራዊ ቡድኖች የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎችን እያደረጉ ይገኛሉ። በምድን አስራ አንድ ከሞሮኮ እና ዚምባቢዌ ጋር የተደለደሉት ደቡብ አፍሪካ እና ለይቤሪያ ዚምባቢዌ ከውድድሩ ውጭ መሆኗን ተከትሎ ወደ አፍሪካ ዋንጫው ለማለፍ ለሦስት ተፋጠዋል። ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖችም የምድብ ሦስተኛ መርሐ-ግብራቸውን መጋቢት 15 በጆአንስበርግ ኦርላንዶ ስታዲየም ያደርጋሉ።

ይህንን ጨዋታ ደግሞ በዓምላክ ተሰማ ከረዳቶቹ ተመስገን ሳሙኤል እና ፋሲካ የኋላሸት እንዲሁም አራተኛ ዳኛው ቴዎድሮስ ምትኩ ጋር በጋራ በመሆን እንዲመሩት ካፍ መመደቡን አውቀናል።

\"\"