በዝናብ ምክንያት የተራዘሙት ጨዋታዎች በቀጣይ ቀናት ይደረጋሉ

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ትናንት እና ዛሬ የተራዘሙት አራት ጨዋታዎች የሚደረጉበት ቀን እና ሰዓት በይፋ ተገልጿል።

\"\"

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በ15ኛ ሳምንት መርሐግብር የመጨረሻ ሁለት ቀናት እንዲደረጉ ቀጠሮ ተይዞላቸው የነበሩት አራት ጨዋታዎች በድሬዳዋ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት መራዘማቸው ይታወሳል። የሊጉ አክሲዮን ማህበር ውድድር እና ሥነስርዓት ኮሚቴ እነዚህን ጨዋታዎች አስመልክቶ ስብስባ የተቀመጠ ሲሆን በመጨረሻም ውሳኔውን ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት የፕሪምየር ሊጉ አክሲዮን ማህበር እንዳሳወቀው ከሆነ በመጪው ማክሰኞ የካቲት 21 10:00 ላይ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሲዳማ ቡና የሚያደርጉት ጨዋታ ከተቋረጠበት ደቂቃ የሚቀጥል ሲሆን ምሽት 01:00 ላይ ደግሞ ኢትዮጵያ ቡና እና ፋሲል ከነማ ይጫወታሉ። በቀጣዩ ቀን ረቡዕ የካቲት 22 10:00 ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ድሬደዋ ከተማ እንዲሁም ምሽት 01፡00 ላይ ባህርዳር ከተማ እና ወላይታ ድቻ የ15ኛ ሳምንት ጨዋታቸውን እንደሚያደርጉም እርግጥ ሆኗል።

\"\"